fbpx
AMHARIC

የነፍሰጡር እናቶች ለተበከለ አየር መጋለጥ በሚወለዱ ህፃናት ላይ የደም ግፊት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል- ጥናት

የአየር ብክለት ለማንኛውም ሰው ጤና አደገኛ ቢሆንም በነፍሰጡርነታቸው ለተበከለ አየር ከተጋለጡ እናቶች የሚወለዱ ህፃናት ላይ የሚያደረሰው ተጽህኖ ከፍ ሊል እንደሚችል እንድ ጥናት አመላክቷል።

በዚህም በነፈሰጡርነታቸው ወቅት ለተበከለ አየር ከተጋለጡ እናቶች የሚወለዱ ህፃናት ከልሎቹ ህፃናት 60 በመቶ ያህል የደም ግፊታቸው ጨምሮ እንደታየ የጥናቱ ጸሀፊ የሆኑት ኑኤል ሙለር ተናግረዋል።

የጥናቱ ተሳታፊዎች ከ1 ሺህ300 እናቶችና ህፃናት ላይ በወሰዱት ናሙና የህጻናቱን የደም ግፊት በተለያዩ ጊዚያት በመለካት ከ 3-9 ዓመት ድረስ ክትትል ማድረጋቸውም ነው የተገለጸው።

በዚህም በነፍሰጡርነት ጊዚያቸው ለተበከለ አየር ከተጋለጡ እናቶች የተገኙ ህፃናት የደም ግፊት ከሌሎቹ ህፃናት አንጻር ጨምሮ ታይቷል ነው የተባለው።

በጥናቱ የአየር ብክለት ለህፃናቱ የደም ግፊት መጨመር ብቸኛ መንስኤ ተደርጎ ያልተወሰደ ሲሆን፥ የህፃናቱ ክብደት፣ የእናቶች ሁኔታ ለልጆች የደም ግፊት መጨመር የእየራሰቸው ሚና ሊኖረቸው እንዳሚችልም ነው በጥናቱ የተጠቆመው።

ተሽከርካሪዎች ከሚጠቀሙት ነዳጅ፣ ከድንጋይ ከሰልና ከማገዶ የሚውጣው ጭስ በውስጡ በአይን የማይታዩ ቅንጣቶች ያሉት ሲሆን፥ እነዚህ ቅንጣቶች በሰዎች መተንፈሻ አካላት ወደ ውስጥ በመግባት ለጤና መታዎክና ብሎም ለሞት የሚዳርጉ ናቸው ተብሏል።

የአየር ብክለቱ በልብና ጭንቅላት አካባቢ የደም መርጋትና መቋረጥ የጤና እንከኖች ሊያጋልጥ እንደሚችልም የዘርፍ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።

የእነዚህ በሽታዎች ምልክቶች በህፃናትም ይሆን ጎልማሳዎች ላይ በሚደረጉ ቅድመ ምረመራዎች የማይታዩ ሲሆን፥ አመጋገብን ማስተካከል፣ ክብደትን መቀነስ፣ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዝወተር ጠቃሚ መሆኑን የአሜሪካ የልብ ጤና ማህበር መረጃ ያስረዳል።

 

ምንጭ፦ upi.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram