ከዐብይ አህመድ የመቶ ቀን የባህር ሀይል ምስረታ ዕቅድ፣ ለግርምት እንዘጋጅ?

ዋዜማ ራዲዮ– ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ደርግ ከአሜሪካ ገዝቷቸው ከነበሩ ሰባት የጦር መርከቦች አራቱን ሽጧቸዋል : ሶስቱን ደግሞ እስካሁን አልተረከባቸውም። ኢትዮጵያ የባህር ሀይል ያስፈልጋታል : በቅርቡም ታቋቁማለች የሚል ንግግር ከመንግስት በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ዘመናዊና የባህር የአየር የየብስና የህዋ ተዋጊ ሀይል ለመገንባት እቅድ እንዳለውና ለዚህም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በዚህ ሳምንት ይፋ አድርገዋል። ኢትዮጵያ…

Advertisements

የቀድሞው ሜቴክ አውሮፕላን ገዝቶ ነበር፣ አሁን የት እንዳለ አልታወቀም

ሁለት መቶ መኖሪያ ቤቶችን በድርጅቱ ገንዘብ ገዝቶ ለግለሰቦች ሰጥቷል ኢትዮ ፕላስቲክ ስልሳ ሚሊየን ብር በአደባባይ ተዘርፏል ዋዜማ ራዲዮ- የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በአዲስ መልክ እንዲዋቀርና በድርጅቱ ውስጥ የተፈፀመው ምዝበራ ተጣርቶ ተጠያቂ ግለሰቦች ህግ ፊት እንዲቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ ምርመራ ከተጀመረ ስንብቷል። በከፍተኛ ምስጢር ተይዞ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እጅግ ግር የሚያሰኙና አዳዲስ መረጃዎችን አግኝቷል። ምርመራው እንደቀጠለ…

አይካ አዲስ በቢሊየን ከሚቆጠር ብድርና ኪሳራ ጋር ወደ ውድቀት እያመራ ነው

ድርጅቱ ከልማት ባንክ የወሰደውን 2.3 ቢሊየን ብር ዕዳ መክፈል አልቻለም በኢትዮጵያ ከስሪያለሁ ቢልም በቡርኪና ፋሶ ግዙፍ ፋብሪካ መገንባት ጀምሯል ዋዜማ ራዲዮ – ኢትዮጵያ ሲገባ በጨርቃጨርቅ ዘርፍ በስራ እድል : በውጭ ምንዛሬ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ብዙ ለውጥ እንደሚያመጣ ተነግሮለት የነበረው የቱርኩ አይካ አዲስ ቴክስታይል ኤንድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደረውን ከ2.3 ቢሊየን ብር በላይ መክፈል…

አንድ ዓይን ያለው በአፈር አይጫወትም! ተወልደ ተባረረ ከሚለው ማን ይተካዋል የሚለው ሊያሳስበን ይገባል

የአገራችን ለውጥ እየተፋጠነ አየር መንገዱን እያነቃነቀ መሆኑ እየተሰማ ነው። ወያኔ በጠመንጃ አስፈራርቶ ከያዘው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማማ ላይ እየተስፈነጠረ እየወደቀ ነው። በፖለቲካ ሹመት ከተያዙ ቁልፍ ቦታዎች አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። በሰው ሃይል አስተዳደርና በሙስና ክስ የሚቀርብበት አቶ ተወልደ እየር መንገዱን ከአቶ ግርማ ዋቄ ተረክቦ ማሳደጉን ግን መካድ አይቻልም። ለማንኛውም ሰሞኑን በየሚዲያው የአየር መንገድ ሃላፊዎች ችግር…

ኻሾግዢ “ሞቷል” – ሳዑዲ አረቢያ

ቱርክ ውስጥ ደብዛው የጠፋው ሳዑዲ አረቢያዊ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ኢስታንቡል በሚገኘው ቆንስላዋ ውስጥ “እዚያ ካገኛቸው ሰዎች ጋር በተፈጠረ ድብድብ ወቅት መሞቱን የምርመራው ቅድሚያ ውጤቶች ያሳያሉ” ስትል ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች። ቱርክ ውስጥ ደብዛው የጠፋው ሳዑዲ አረቢያዊ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ኢስታንቡል በሚገኘው ቆንስላዋ ውስጥ “እዚያ ካገኛቸው ሰዎች ጋር በተፈጠረ ድብድብ ወቅት መሞቱን የምርመራው ቅድሚያ ውጤቶች ያሳያሉ” ስትል…

የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን

የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን (Vulvovaginal yeast infection) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምንድን ነው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ላይ የመቆጣት እና የማሳከክ ስሜት የሚያስከትል ኢንፌክሽን ነው። ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዳ(candida) በመባል በሚጠራው የፈንገስ ዝርያ ነው። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶችና የህመም ስሜቶች ምንድን ናቸዉ? ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ ● የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ…

ድሬዳዋ ፖሊስ ለ13 ሰዎች ህልፈትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ግጭት የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ሐምሌ 29 2010 ዓ.ም ለ13 ሰዎች ህልፈትና ለንብረት መውደም ምክንያት በሆነው ግጭት ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ውጤት ዛሬ ይፋ አድርጓል። ኮሚሽኑ ዛሬ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥ በእለቱ በተፈጠረው ሁከት በ3 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የ13 ንፁሀን ዜጎች ህይወት ማለፋንና በ42 ቤቶች ላይ ቃጠሎና ዝርፊያ መካሔዱን ገልጿል። ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራ 4 ግለሰቦች…

የአክሱም ሆቴሉ ቡድን የሚዲያ ውጊያ ክተት

መቀሌ የሚገኘው አክሱም ሆቴል የቪአይፒ ክፍሎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከመንግስት ሀላፊነት በጡረታ በተወገዱ በህወሀት ነባር ታጋዮች ተሞልቷል፡፡ እነዚህ የቀድሞ ባለስልጣናት ከጦር ሰራዊት፣ ከደህንነት ወይም ከከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ተነስተው በዚህ ለወትሮው በቱሪስቶች ማዘውተሪያ ቦታ የመሸጉት የለመዱትን ውስኪ ለመጨበጥ አመቺ ስፍራ ስለሆነ ብቻ አይደለም፡፡ በዚህ ሆቴል ውስጥ የኢትዮጵያን ፖለቲካ አቅጣጫ ሊለውጥ የሚችል አጀንዳን ያነሳሉ/ይጥላሉ፡፡ በቀደሙት ጊዜያት ሲያሾሯት…

ኢትዮ ቴሌኮም በ47 የአጭር ቁጥር ጽሁፍ መልዕክት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

ኢትዮ ቴሌኮም የህብረተሰቡን ቅሬታ መሰረት አድርጎ በ47 የአጭር ቁጥር ጽሁፍ መልእክት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ። የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ እርምጃው የተወሰደው ከህብረተሰቡ በሚነሳው ቅሬታ ላይ ተመስርቶ ነው። አቶ አብዱራሂም፥ ከአጭር ቁጥር (Short code) የጽሁፍ መልእክት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ከደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎች አሉ ብለዋል። ከቅሬታዎቹ መካከል…

ንግድ ባንክ ባለፉት 11 ቀናት ከ42 ሚሊየን ዶላር በላይ መመንዘሩን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 11 ቀናት ከ42 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማካሄዱን ገለጸ። የአዋሽ ባንክም ባለፉት አስራ አራት ቀናት ከ10 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማካሄዱን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግለሰቦች የያዙትን የውጭ ሀገር ገንዘብ በባንክ እንዲመነዝሩ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በባንክ እየተካሄዱ ያሉ የውጭ አገራት መገበያያ ገንዘቦች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የኢትዮጵያ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram