fbpx
AMHARIC

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ተደራዳሪ ቡድን ነገ አዲስ አበባ ይገባል

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ተደራዳሪ ቡድን ነገ ጠዋት አዲስ አበባ እንደሚገባ መንግስት ገለፀ።

የድርጅቱ ተደራዳሪ ቡድን ወደ አዲስ አበባ የሚመጣው የኢፌዴሪ መንግስት መቀመጫውን ከሀገር ውጭ ካደረገውና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴግ) ጋር ድርድር መጀመሩን ተከትሎ ነው።

የድርጅቱ ተደራዳሪ ቡድን ወደ አዲስ አበባ መምጣትም የድርድሩ አካል መሆኑን ነው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፀው።

የኢፌዴሪ መንግስት በቅርቡ መቀመጫውን ከሃገር ውጭ ካደረገውና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴግ) ጋር ድርድር እንደጀመረ መግለጹ ይታወሳል።

የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች መቀመጫውን ከሃገር ውጭ ካደረገውና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴግ) ጋር ድርድር ማድረጋቸውንም ፅህፈት ቤቱ ከዚህ ቀደም ገልጿል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram