fbpx
AMHARIC

በህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም ኃይል ለማመንጨት ዕቅድ አለ

ዮሐንስ አንበርብር – ሪፖርተር

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም 2011 ዓ.ም. ኃይል እንዲያመነጩ ዕቅድ መያዙን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ።

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት የሁለቱን ተርባይኖች ተከላ ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ በመሆኑም በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም.ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ ዕቅድ ተይዟል። ሁለቱን ተርባይኖች ለማስጀመር ግድቡን በውኃ መሙላት የሚጠይቅ አለመሆኑን የገለጹትምንጮች፣ ግንባታው እየተከናወነ ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት እንዲችሉ የሚያስፈልገውን የውኃ መጠን ማግኘት እንዲቻል ተደርጎ የግንባታ ዲዛይኑመሠራቱን ገልጸዋል።

ግድቡ በአጠቃላይ 16 ተርባይኖች ሲኖሩት፣ በቅድሚያ ኃይል እንዲያመነጩ የታቀዱት ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅምአላቸው። በመሆኑም በመጪው መስከረም አገሪቱ ተጨማሪ 750 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ስለምታገኝ፣ ይህም ጣና በለስና ተከዜ የኃይል ማመንጫግድቦች ተደምረው በአሁኑ ወቅት ከሚያመነጩት የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን እንደሚበልጥ አስረድተዋል።

ግድቡ ሲጠናቀቅ 6,450 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖረው፣ ይህም አሁን በአገሪቱ ያለውን ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ወደ11 ሺሕ ሜጋ ዋት ኃይል ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የህዳሴው ግድብ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ ላይ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው፣ የአገሪቱን የኃይል ሥርጭት ከ41 በመቶ ወደ 75 በመቶ እንደሚያደርስምጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

የህዳሴ ግድቡ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የሚይዝ በመሆኑ፣ ከዓባይ ተፋሰስ አገሮች በበለጠ ለዘመናት በብቸኝነት የወንዙ ተጠቃሚ የሆነችው ግብፅየውኃ ድርሻዋ እንዳይቀንስባት ሥጋቷን እየገለጸች ነው፡፡

ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ ጥቅም ላይ ለማዋል ስትነሳም ሆነ እስካሁን የምታስረዳው በሌላ የተፋሰሱ ተጠቃሚ አገር ላይ ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርህንነው፡፡ የግድቡን የውኃ አያያዝና አለቃቀቅ የተመለከተ ጥናትም በገለልተኛ አጥኚ ቡድን እንዲካሄድ መወሰኗም ይታወቃል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት በህዳሴ ግድቡ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ጉዳይ ውይይቱ አሁንም እንደ ቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ባለሙያዎችከመጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሱዳን ምክክር በማድረግ ላይ ነበሩ፡፡ የውይይቱ ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሦስቱም አገሮች መሪዎችእንደሚቀርብ ይጠበቃል።

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram