fbpx
AMHARIC

Health Benefits of Walking – በየቀኑ የእግር ጉዞ ማድረግ የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የተለያዩ ጠቀሜታዎች ያስገኛል፤ ይሁን እንጂ ከባድ መሆን እንደሌለበት ባለሙያዎች ይመክራሉ።

በየቀኑ ከቤት ዉጪ ቀላል የእግር ጉዞ ማድረግ ደግሞ የአእምሮ ውጥረትና ተፅእኖዎችን በመቀነስ ብዙ የጤና ጠቀሜታዎች ለማግኘት ይረዳል።

ይህም ተመራማሪዎቹ “ሰዎች የእግር ጉዞ የማድረግ ባህሪ በማዳበር የሚያገኙዋቸው ጥቅሞች አሉ” ያሉ ሲሆን፥ ጥቅሞቹንም እንዲህ ገልፀዋቸዋል።

ጥሩ ስሜት ለመፍጠር

በአውሮፓውያኑ 2016 የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ምንም ሳያውቁ ወይም ያለፕሮግራም የሚደረግ የእግር ጉዞ ውስጣዊ ስሜት ለማሻሻል ይረዳል።

በተጨማሪም ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብለው ከሚውሉት ወንበር ተነስተው እግርዎን እንዲያፍታቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።

ባለሙያዎቹ በየቀኑ የእግር ጉዞ ለማድረግ በእቅድ የሚያከናውኑት ከሆኑ ደግሞ ከዚህ በበለጠ ጥቅሞች እንዳሉት መክረዋል።

ይህም ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት ከቤት ውጪ የሚደረግ የእግር ጉዞ ውጥረትን ለማቅለል ይረዳል።

ጥናቱ 90 ደቂቃ በእግር መጓዝ የጀመሩ የጥናቱ ተሳታፊዎች ለራስህ የሚደረጉ አሉታዊ አስተሳሰቦች እና ከአእምሮ ሕመም ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች በመቀነስ ጥሩ ስሜት እንዲኖራቸው ማድረጉ አንስቷል።

ለልብ ጤንነት

ጥናቱ እንደሚያሳየው መካከለኛ የእግር ጉዞ ማድረግ የልብ ጤንነት በመጠበቅ አተነፋፈሳችን እንዲሻሻል ያግዛል።

ለዚህም የአሜሪካ የልብ በሽታ ማህበር እንደሚለው ከሆነ፥ በቀን ውስጥ 30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ የደም ግፊትን ለማሻሻል፣ የልብ ህመም እና የስትሮክ በሽታ አደጋ ለመቀነስ ይረዳል።

የምንወስደውን የጣፋጭ ምግቦች መጠን እንድንቀንስ ያግዘናል

የ15 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ ሰዎች የጣፋጭ ምግብ ፍላጎታቸው በግማሽ ይቀንሳል።

ይህም በጣፋጭ ምግቦች ምክንያት የሚመጣውን በሽታ ለመከላከል ይረዳል ማለት ነው።

የአእምሮ ጤናን ያሻሽላል

የእግር ጉዞ ማድረግ አእምሮን ጤናማ እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ አዳዲስ ነገሮች የመፍጠር እና የማዳበር ችሎታን ያዳብራል።

ይህም ቀላል እና ከፍተኛ የአእምሮን የመርሳት ችግር እክልን በግማሽ ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል ነው የተባለው።

ለዚህም በየሳምንቱ በአጠቃላይ 72 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ በእግር የተጓዙ ሰዎች የመገንዘብ ችሎታቸው ከሚጎዱ በሽታዎች በግማሽ አደጋው ይቀንሳል።

 

 

 

ምንጭ፦ www.health.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram