fbpx

መከላከያ ከባድ የጦር መሳሪያዎቹን ከዛላምበሳ ድንበር ማንቀሳቀስ አልቻለም

ትናንት ሰኞ አመሻሽ ላይ ከኢትዮ ኤርትራ ድንበር አከባቢ ከባድ የጦር መሳርያ ይዘው የሚንቀሳቀሱ የመከላከያ ሠራዊት መኪኖች በአካባቢው ባሉ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገዋል። በድንበር አካባቢ ያሉት ሰዎች ይህንን የሠራዊቱን ከባድ የጦር መሳሪያ የማንቀሳቀስ እርምጃን ያስተጓጎለው መስከረም ወር ላይ የተከፈተው የዛላምበሳና የራማ አገናኝ የድንበር መተላለፊያዎች ላይ የኤርትራ መንግሥት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ቁጥጥር ማድረግ ከመጀመሩ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ስጋት…

“በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም” ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ

የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑትና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተናቸው በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል። ቢቢሲ አማርኛ፡ አንዳርጋቸው ታፍኖ መወሰዱን ባወቅክባት ቅፅበት ምን ተሰማህ? ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ፡ አንዳርጋቸው የተያዘ ጊዜ ኒው ዮርክ ነበርኩ። እንደተያዘ እዚያው የመን እያለ ነው የሰማሁት፤ በተያዘ በግማሽ ወይንም በአንድ ሰዓት አብረው ሲበሩ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ…

“የኦነግ ሥራዊት በሙሉ ተጠሪነቱ፣ የሚመራውም፣ ትዕዛዝ የሚቀበለውም ከኦነግ ሊቀመንበር ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ነው።” በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ጃል መሮ

በኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትን አንግሷል። ይህን ብቻ አይደለም በቅርቡ በክልሉ ውስጥ ለሚፈጸሙ ግድያዎች እና ዘረፋዎች መንግሥት ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል። በቅርቡ የክልሉ ፖሊስ እና ባለስልጣናት በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ኦነግን የአከባቢው አስተዳደሮችን ይገድላል፣ ጦር መሳሪያ ይዘርፋል እንዲሁም ሚሊሻዎችን ትጥቅ ያስፈታል ሲሉ ከሰዋል። ኩምሳ ዲሪባ ወይም በትግል ስሙ…

የወጋገን ባንክ ድንገተኛ አንድ ቢሊየን ብር ትርፍ እያነጋገረ ነው

ዋዜማ ራዲዮ፡ ሰሞኑን ንግድ ባንኮች ያለፈ አመት ሂሳባቸውን እያወራረዱ ትርፋቸውን ይፋ የሚያደርጉበት ነው።ወጋገን ባንክም ባደረገው የባለ አክስዮኞች ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ባንኩ 1.05 ቢሊየን ብር ትርፍን ከታክስ በፊት ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።ይህም ባለፈው አመት ካገኘው ትርፍ በ50 በመቶ ብልጫ ያለው እንደሆነ ገልጿል። በትርፍ ቢሊየን ብርን በመቀላቀል በግል ንግድ ባንኮች ታሪክ አዋሽና ዳሽን ባንክን ተከትሎ ሶስተኛ ሆኖ መግባቱም…

በኤርትራ ውስጥ የታቀደው መፈንቅለ መንግስት ከሸፈ

በAdane Atana የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ ካድሬዎች ከ3 ሳምንት በፊት ጀምረው ኤርትራ ውስጥ የወያኔ ድጋፍ ያለው መንግስታዊ ለውጥ እንደሚደረግ ያለሃፍረት ጉራ በተሞላበት እርግጠኛ ሆነው በየመሸታ ቤቱ ሲወሸክቱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ እኒሁ የወያኔው የቀን ጅብ ካድሬዎች እንዳውም ይባስ ብለው የጀኔራል ስብሃት ኤፍሬምን ፎቶ በመለጠፍ ምስጋናቸውን/አድናቆታቸውን መግለጽ ጀምረው ነበር፡፡ ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም የትግሬ ወያኔን ባዶ ህልም…

የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል ተግባርና ኃላፊነቶች ምንድን ናቸው?

ዮሐንስ አንበርብር እሑድ ታኅሳስ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ መቋቋሙ የተገለጸውና ‹‹የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው ወታደራዊ ኃይል፣ የተሰጠውን ኃላፊነት በመወጣት ረገድ ያደረገውን ዝግጅትና ብቃት የሚያሳይ ወታደራዊ ትርዒት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ለሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት አሳይቷል። የአባላቱን የብቃት ደረጃ ለማሳየት ወታደራዊ ትርዒት ያቀረበው የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል የመከላከያ…

የመከላከያ ሠራዊትን ሀብትና ንብረት ወደ ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት የሚያስገባው አዋጅና አዳዲስ ድንጋጌዎቹ

ዮሐንስ አንበርብር መንግሥት በ2004 ዓ.ም. ከመደበው በጀት ውስጥ ከ6.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነውን ወጪና ገቢ ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉን፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር በ2005 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ይፋ ማድረጉ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሶ ነበር። በወቅቱ በቀረበው ሪፖርት መሠረት ዘጠኝ መሥሪያ ቤቶች 3.5 ቢሊዮን ብር ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ማድረጋቸው ተጠቅሷል። ከዚህ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የያዙት…

በትግራይና አማራ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚደረጉ ውድድሮችን በሰላማዊ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል- ዶ/ር ደብረፅዮን

በትግራይና አማራ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚደረጉ ውድድሮችን በሰላማዊ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። ባለፈው ዓመት በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት በትግራይና አማራ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች መካከል ሲካሄድ የነበረው ውድድር በገለልተኛ ሜዳ ሲስተናገድ መቆየቱ ይታወሳል። ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሁለቱ ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች ጋር ባደረገው…

የትግራይ ወጣቶች በስማችሁ የሚነግዱ እና የጉዞ አድዋ ተጓዦችን ወዮላችሁ የሚሉ አክቲቪስቶችን …

የትግራይ ወጣቶች እናንተን የማይመስሉ፤ በስማችሁ የሚነግዱ እና የጉዞ አድዋ ተጓዦችን ወዮላችሁ የሚሉ አክቲቪስቶችን አደብ አስገዙዋቸው፡፡ የህወሃት አክቲቪስቶች ለትግራይ ህዝብ እንደማያስቡ ለማወቅ መቀሌ ሹም ጭን ስር ተቀምጠው ትግራይን እረግጣለሁ የምትል ሞክረኝ ይላሉ፡፡ የእነሱ ምኞት አጻፋው በሌላው ኢትዮጵያ ክፍል ተጋሩ ላይ እንዲፈጸም ነው፡፡ ይሄንን ለዘለዓለም አያዩትም፡፡ *** ከስናፍቅሽ አዲስ ጉዞ አድዋ ዘንድሮም በድምቀት ይካሄዳል፡፡ የአድዋ ተጓዦች ዝግጅታቸውን…

ኤምባሲው አሜሪካ በዶ/ር አብይ ምርጫ እጇን አስገብታለች የሚለውን የህወሀት ክስ “መሰረተ ቢስ” ሲል አጣጣለ

የህወሀት ባለ ስልጣናት ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን እንዲመጡ ያደረገችው አሜሪካ ናት በማለት መናገራቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳዩን “መሰረተ ቢስ” ሲል አጣጥሎታል። ቪኦኤ ሆርን ኦፍ አፍሪካ እንደዘገበው ባለፈው ሳምንት በመቀለ በተካሄደው ኮንፈረንስ ላይ የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ “የዶ/ር አቢይ ወደ ስልጣን መምጣት የአሜሪካ ምርጫ ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram