fbpx
AMHARIC

ለመስጠትም ሆነ defend ለማድረግ እጅግ ፈታኝ የሆነ ነገር!

Benefit of doubt ለመስጠትም ሆነ defend ለማድረግ እጅግ ፈታኝ የሆነ ነገር!

የሞያሌውን ግድያ ለማውገዝ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፤ የእግር ኳስ ዳኛ እንኳን የቅጣት ምት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ከመስመር ዳኞች ጋር ለአፍታ ይመክራል

በ ዳዊት ከበደ – Awramba Times

አእምሮው ያልተቃወሰ ማንም ጤናማ ዜጋ እንደሚያስበው ሁሉ፣ እኔም ማንም የበላይ ማንም የበታች ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ኢትዮጵያን ማየት እሻለሁ። ከዚህ አንፃር አሁን ያለው ስርአተ መንግስት ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል ብዬ ስለማምን (በርግጥም አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የተሻለ የተደራጀ አካልም ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ) ይህ ስርአት እንከኖቹን አርሞ መራመድ ከቻለ ለዛሬዋ ኢትዮጵያ (የነገውን ባላቅም) ቢያንስ በዚህ ሰአት ከሱ የተሻለ መንግስት ሊመጣ ይችላል ብዬ አላስብም።

ከዚህ ጎን ለጎን ከብዙ መመዘኛዎች አንፃር ኢህአዴግ ለዜጎቹ ክፉ የሆነ ገዢ ፓርቲ ነው ብዬም አላምንም። ለዛም ነው በተቻለ መጠን በተለይ ባለፉት አምስት አመታት ስርአቱን ከመንቀፍ ይልቅ (በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ የስርአቱ አፈቀላጤነት ታርጋ እስኪለጠፍብኝ ድረስ) defend በማድረግ ያጠፋሁት ጊዜ እጅግ የሚበዛው።

ያፈጠጡ ያገጠጡ ስህተቶች ቢኖሩ እንኳን በተቻለ መጠን ድምዳሜ ላይ ከመድረስ ይልቅ ለ benefit of doubt ቅድሚያ መስጠትን ነበር የማስቀድመው። ለምሳሌ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባለፈው ሳምንት ለፓርላማ ሲቀርብ ድጋፌን እዚሁ በይፋ ገልጫለሁ ምክንያቴ ደግሞ ከስርአተ መንግስቱ ህልውና ጋር የተያያዘ ለዜጎች ህይወት የሞት የሽረት ጉዳይ ነው ብዬ ስለማምን ነው።

ዛሬ ግን ለbenefit of doubtም ሆነ defend ለማድረግ እጅግ ፈታኝ የሆነ ነገር ገጠመኝ። ይህ ሁሉ መንደርደሪያ መዳረሻዬን ሞያሌ ላይ ለማድረግ ነው።
በሞያሌ የተፈፀመው ግድያ ለማውገዝ ሰው መሆንና እንደ ሰው ማሰብ ብቻ በቂ ነው። የእግር ኳስ ዳኛ እንኳን የቅጣት ምት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ከመስመር ዳኞች ጋር ለአፍታ ይመክራል፤ ደርዘን ያህል መተኪያ የሌለው የሰው ልጅ ህይወት ረግፎ “በመረጃ ስህተት ተፈፀመ” ብቻ ብሎ ማለፍ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት ሊኖረው አልቻለም፤ እውነቴን ነው ፍጹም ሊዋጥልኝ አልቻለም። በበኩሌ የሻለቃዋ አዛዥና በግድያው የተሳተፉ ሰዎችን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ በቂ አይደለም።

ከዚህ ድርጊት ጀርባ አንድ ተልእኮ ያነገበ አካል (ከየትኛውም ብሄር ሊሆን ይችላል) እንዳለ እንዲሁ instinct ቴ ይነግረኛል። መግለጫዎቹን ደጋግሜ ለማየት ሞከርኩ በየትኛውም ሚዛን ላይ ባስቀምጠው ባወጣው ባወርደው ፈፅሞ ሊዋጥልኝ አልቻለም። የመረጃ ስህተት ተብሎ የቀረበው ምክንያትም ሊያሳምነኝ አልቻለም። የቱን ያህል የተሳሳተ መረጃ ቢደርስህ አልመህ የምትተኩስበት አካል እንዳልታጠቀ ካረጋገጥክ በቃ ቃታውን አለመሳብ እኮ ነው።

አዋጁ ለዜጎች ዋስትና ይጠቅማል ብለን በይፋ ደገፍነው
እነ ጃዋር ደግሞ ዜጎች እንዲገደሉ የሚያደርግ አዋጅ ነው አሉ። እንግዲህ አሁን የሆነው ነገር ደግሞ እዩት። እነ ጃዋር ሁሌም ግብ እንዲያስቆጥሩባችሁ እንዴት ሁኔታዎችን ራሳችሁ እንድምታመቻቹ አያችሁት? ከሱ በላይ ግን ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወት መቀጠፉ ያሳዝናል።

አንድ ልክ ያልሆነ ነገርማ አለ!
በድጋሚ ለሟቾች ነፍስ ይማር

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram