ጓቲማላ የእስራኤል ኤምባሲዋን ከቴልአቪቭ ወደ ኢየሩሳለም አዞረች

ጓቲማላ ከአሜሪካ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ ሀገር በመሆኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጓቲማላ ፕሬዝዳንት ጂሚ ሞራሌስን ማመስገናቸው ተሠማ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ግብጽ ፣ደቡብ አፍሪካ፣ቱኒዚያ ፣ቱርክ እና ሌሎች የአረብ ሀገራት እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ ሰሞኑን በፈጸመችው ግድያ ቁጣቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ 
እስራኤል በመንግስትነት ከተመሰረተች እኤአ ከ1948 ጀምሮ ኢየሩሳሌም የፍልስጤምም ሆነ የእስራኤል መናገሻ ከተማ ሳትሆን እስካሁን ቆይታለች፡፡

አሁን ኢየሩሳሌም በዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ የእስራኤል ዋና ከተማ ለመሆን በመታጨቷ አሜሪካ እና ጓቲማላ ኤምባሲያቸውን ከቴል አቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም በይፋ ማዞራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Share your thoughts on this post