የጃፓን የባቡር ኩባንያ ከመነሻው 25 ሰከንድ ቀድሞ በመጓዙ ተሳፋሪዎችን ይቅርታ ጠየቀ

የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ኩባንያው በደንበኞቻችን ላይ የፈፀምነው ጥፋት ከባድና ይቅር የማይባል ቢሆንም ይቅርታ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ነው ያለው።

ከኖቶጋዋ ጣቢያ የሚነሳው 7 ሰዓት ከ12 ቢሆንም የባቡሩ ኦፕሬተር የመነሻ ሰዓት አድርጎ ያሰበው 7 ሰዓት ከ11ን በመሆኑ ምክንያት 7 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ላይ ጉዞውን ለመጀመር ተገዷል። በዚህም ባቡሩ ከመነሻ ሰዓቱ 25 ሰከንዶችን ቀድሞ በመጓዙ ኩባንያው ታላቅ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ፥ወደፊት ይህ ስህተት አይለመደኝም ብሏል።

የባቡር ኦፕሬተሩ በሮችን ዘግቶ መጓዝ እንደጀመረ ከመነሻ ሰዓቱ ቀድሞ መነሳቱን ቢያውቅም ከመፀፀት ውጪ ሌላ እድል አልነበረውም ነው የተባለው።

ምንጭ፦www.stuff.co.nz እና ቢቢሲ

Share your thoughts on this post