የእስራኤል የጦር ጄቶች በሰሜናዊ ጋዛ ድብደባ መፈፀማቸው ተነገረ

የእስራኤል የጦር ጄቶች በሰሜናዊ ጋዛ በዛሬው እለት ማለዳ ላይ ድብደባ መፈፀማቸው ተሰምቷል። የጦር ጄቶቹ ድብደባ በተለይ የፊሊስጤም አስተዳደር ውስጥ የምትገኘዋን ቤት ላሂያ የተባለችውን ከተማ ኢላማ ያደረገ እንደነበረም ተነግሯል።

የጋዛ የጤና ሚኒስቴር እንጋስታወቀው፥ በአየር ድብደባው እስካሁን አንድ ሰው ላይ ብቻ ጉዳት አድርሷል። በአውሮፕላን የተካሄደውን ድብደባ ተከትሎ የእስራሌል ጦር እንደገለፀው፥ ድብደባው የሀማስ ለተተኮሱ የከባድ የጦር መሳሪያ ጥቃት መልስ ለመስጠት ነው። የእስራኤል ጦር በተለያዩ ጊዜያት በጋዛ ሰርጥ ላይ የአውሮፕላን ጥቃቶችን መፈፀሙ ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.presstv.com

Share your thoughts on this post