ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ቦምብ ፈነዳ

በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ትላንት ምሽት ፍንዳታ መድረሱን የዓይን እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።

ዋሺንግተን ዲሲ —
በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ትላንት ምሽት ፍንዳታ መድረሱን የዓይን እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።

ይህንኑ ያረጋገጠው የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ማብራሪያ አልሰጠም።

ትላንት ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ከዓለም ካፌ ፊት ለፊት የደረሰው ይህ ፍንዳታ ለጊዜው ከፍተኛ መደናገጥ ፈጥሮ እንደነበር እነዚሁ ያይን እማኞች አስረድተዋል።

ፍንዳታውንና የፈጠረውን መደናገጥ ባይናቸው ከተመለከቱት መካከል የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ የወጣቶች ሊግ አመራር አባል አቶ አዲሱ ቡላላ አንዱ ነው።

Share your thoughts on this post