በህገወጥ መንገድ በሱዳን በኩል ሲገቡ የነበሩ ከ350 በላይ ሽጉጦች ተያዙ

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

መሳሪያዎቹ በሱዳን በኩል አብደራፊንን አቋርጠው ሊገቡ ሲሉ ነዉ በትግራይ ክልል ፀገዴ ወረዳ መንደር አውሮራ አካባቢ ዛሬ ማምሻዉን በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የፀገዴ ወረዳ የጸጥታ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሻምበል እሸቴ አወቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በክልሉ የፀጥታ ሀይል እና በመከላከያ ሰራዊቱ ከፍተኛ ትብብር 355 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

መሳሪያዎቹ የተጫኑበት ኮድ 3 -03988 የሆነ ኤፍ ኤስ አር የጭነት መኪና እና ረዳት ሹፌሩም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑም ነው የተመለከተው።

በሰለሞን ገብሩ – ኤፍ ቢ ሲ

Share your thoughts on this post