fbpx

80 ሺህ ሴቶችን ለትዳር ጠይቆ ያልተሳካለት ቻይናዊ

ቻይናዊው ባለፉት ስምንት ዓመታት የምትወደድ የትዳር ጓደኛን ለማግኘት 80 ሺህ ሴቶች ለማግኘት ቢቀጥርም ጥያቄው በ80 ሺዎቹ ውድቅ ተደርጎበታል።

የ31 ዓመቱ ቻይናዊ የትዳር ጓደኛን ለማግኘት እጅግ ከመጓጓቱ የተነሳ በቀጠሮ ያበዳ የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቶታል።

ግለሰቡ በ2013 በቤጂንግ ጎዳናዎች የትዳር ጎደኛ እንደሚፈልግ የሚያሳይና ፎቶን ይዞ በመዞርና ምስሉን በማህበራዊ ድህረገፆች በመለጠፍ ትዳር እንደሚፈልግ ማስታወቂያ በመስራት እንደሚታወቅ ተገልጿል።

ግለሰቡ በአሁን ወቅት ግን የትዳር ጓደኛ እንደሚፈልግ የሚያሳይ ምስል ሳይለጥፍ በአዲስ መልኩ በድረ ገፆች፣ በማህበራዊ የመልዕክት መለዋወጫዎች ከሴቶች ጋር ጎደኝነትን በመፍጠር እና ሴቶን በመንገድ ላይ በሚያገኝበት ወቅት የትዳር ጥያቄ እንደሚያነሳና ሴቶችም ጥያቄውን በተደጋጋሚ ውድቅ እንደሚያደርጉበት ተገልጿል።

የቅርብ ሰዎቹ ለዚህ ምክንያቱ ግለሰቡ ሴቶችን ለትዳር የሚጠይቅበት መንገድ ጠንከር ያለ መሆኑ እና ለሴቶች በማይመች መልኩ በመሆኑ እንዳልተሳካለት ይናገራሉ።

ግለሰቡ በበኩሉ ጥያቄዎቹ ውድ የሚሆኑበት የተለየ ምክንያት እንዳለው ነው የሚገልፀው።

በአሁን ወቅት ያሉ ሴቶች የፍቅር ጎደኛን የሚመርጡበ ቆንጆ ወንድ እና ሲያወራ እነሱን ሊማርክ የሚችል መሆኑን የገለፀ ሲሆን፥ አጭር ፣ ቆንጆ ባለመሆኑና ሴቶችን ለማስደሰት አለመዋሸቱ ጥያቄ ተቀባይነት እንዳያገኝ ምክንያት እንደሆኑ ተነግሯል።

ግለሰቡ 80 ሺህ ጊዜ ያቀረበው የትዳር ጥያቄ ውድቅ መሆኑን በቪዲዮ በድረ ገፆች ማውጣቱን ተከተሎ የሀገሪቱ ሚዲያዮች እውነትነቱ ያጠራጠራቸው ሲሆን፥ ይህንኑ ለማጣራት ጥረት እያደረጉ ነው ተብሏል።

የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ተጠቃሚዎችም በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ግለሰቡ የትዳር ጥያቄ የሚያቀርበት መንገድ ትክክል አለመሆኑ እንጂ ቁመቱና መለኩ በምክንያትነት ሊጠቀስ አይችልም ብለዋል።

ምንጭ፦ ኦዲቲሴንትራል

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram