fbpx

8ኛው የኢትዮ-አሜሪካ የሰብዓዊ መብትና ዴሞክራሲ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

8ኛው ኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሰብዓዊ መብትና ዴሞክራሲ ምክክር መድረክ በዛሬው እለት አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነርን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የጋራ ምክክር በሰብዓዊ መብት፣ በዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ነው ትኩረቱን አድርጎ እየተካሄደ የሚገኘው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል፥ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥበቃ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን በማስፋት ረገድ ቀጣይነት ያለው ለውጥ እየመጣ ነው ብለዋል።

በተለይም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፍትህ ስርዓት ረገድ መንግስት የተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ነው ዶክተር አክሊሉ ያብራሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት እንዲከበር እና የዴሞክራሲ ምህዳሩ እንዲሰፋ ታላላቅ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸውንም ዶክተር አክሊሉ አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ረይነር በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብት እንዲከበር እና የዴሞክራሲ ምህዳሩ እንዲሰፋ ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል።

በተለይም መንግስት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ምህዳሩን ለማስፋት የወሰዳቸው እርምጃዎች ዳያስፖራው በሁሉም መስክ እንዲሳተፍ በር ይከፍታል ነው ያሉት።

የአሜሪካ መንግስት አሁን እየታዩ ለውጦች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አምባሳደር ማይክል ራይነር አረጋግጠዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram