fbpx
AMHARIC

44 ኪሎ የሚመዝን የማህጸን እጢ በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሙያተኞች በቀዶ ህክምና ተወገደ

ንጋትዋ የ40 ዓመት ሴት ናት፡፡ ባጋጠማት የማህጸን እጢ(Ovarian Tumor) ምክንያት የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ መጣች፡፡ በማህጸንዋ አካባቢ በተፈጠረው እጢ ምክንያት በትክክል ቆማ መሄድ አልቻለችም ፡፡ ጎብጣ ነበር፡፡ እጢው ከመተለቁ የተነሳ ወደ ውጭ የተዘረገፈ የውስጥ አካል ያላት ይመስላል፡፡ በሰውነትዋ ላይ መታየት ከጀመረ ሶስት ዓመት ቢሞላውም የሀኪምን ዳጃፍ መርገጥ አልፈለገችም፡፡ ምርጫዋ ያደረገችው የባህል መድኃኒትን ነው፡፡ ይሁን እንጂ መጠኑ ግን መጨመሩን አላቆመም፡፡


በዶ/ር ቤተል ደረጀ የሚመራ የባለሙያዎች ቡድን ለንጋትዋ አራት ሰዓት የፈጀ ቀዶ ህክምና ካደረጉላት በኋላ 44 ኪ.ግራም( አርባ አራት ኪሎ ግራም) የሚመዝን እጢ ከማህጸኗ አካባቢ አውጥተውላታል፡፡ ንጋትዋ ከቀዶ ህክምናው በኋላ ጤንነት እንደተሰማት ገልጻለች፡፡አሁን የሰውነትዋ ክብደት 53 ደርሷል፡፡


ዶ/ር ቤተል እንደሚሉት ንጋትዋ ከአሁን በኋላ ቀሪ ዘመንዋ ብሩህ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ቀድማ ሃኪም ዘንድ ብትመጣ 44 ኪሎ የሚመዝን እጢ ተሸክማ አትቆይም ነበር ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- St. Paul’s Hospital Millennium Medical College-SPHMMC

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram