fbpx

31ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

የአፍሪካ ህብረት 31ኛው የመሪዎች ጉባዔ በሞሪታኒያ ዋና ከተማ በናውክቾች በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀመረ።

በሞርታኒያ “ሙስናን ማሸነፍ ለአፍሪካ ዘላቂ ለውጥ እውን መሆን ወሳኝ ነው” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የመሪዎች ጉባዔ የአህጉሩ ሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም ነፃ የንግድ ቀጠና የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል ተብሏል።፡

የህብረቱ ሙሳ ፋቂ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በየዓመቱ ከ50 ቢሊዮን ዶላር የሚልቅ ገንዘብ ወይም ኃብት በህገ ወጥ መንገድ ከአፍሪካ ሀገራት እንደሚሸሽና ገንዘቡ በሚሊየን አፍሪካዊያንን ከድህነት ለማውጣት የሚያስችል ነው ተናግረዋል።።

በመሆኑም አፍሪካዊያን የተለያዩ የሙስና ተግባራትን ለመግታት ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው ያሳሰቡት።

በዚህ የመሪዎች ጉባዔ በሳህል አካባቢ፣በምዕራብ ሳህል በፖሊሳሪዮ እና በሞሮኮ መካከል ያለው ግጭት ዋነኛ የውይይት አጀንዳ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

ከዚህ በላፈ በዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ፣ ህገ ወጥ ስደት እና በትብብር ወንጀል መከለከል በሚቻልበት ሁኔታ ትኩረት ያደርጋሉ።

በሞሪታኒያ እየተካሄደ በሚገኘው 31ኛው የመሪዎች ጉባዔ የ22 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram