ኢትዮ ቴሌኮም በ47 የአጭር ቁጥር ጽሁፍ መልዕክት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

ኢትዮ ቴሌኮም የህብረተሰቡን ቅሬታ መሰረት አድርጎ በ47 የአጭር ቁጥር ጽሁፍ መልእክት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ። የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ እርምጃው የተወሰደው ከህብረተሰቡ በሚነሳው ቅሬታ ላይ ተመስርቶ ነው። አቶ አብዱራሂም፥ ከአጭር ቁጥር (Short code) የጽሁፍ መልእክት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ከደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎች አሉ ብለዋል። ከቅሬታዎቹ መካከል…

Advertisements

ንግድ ባንክ ባለፉት 11 ቀናት ከ42 ሚሊየን ዶላር በላይ መመንዘሩን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 11 ቀናት ከ42 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማካሄዱን ገለጸ። የአዋሽ ባንክም ባለፉት አስራ አራት ቀናት ከ10 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማካሄዱን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግለሰቦች የያዙትን የውጭ ሀገር ገንዘብ በባንክ እንዲመነዝሩ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በባንክ እየተካሄዱ ያሉ የውጭ አገራት መገበያያ ገንዘቦች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የኢትዮጵያ…

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 34 ተጫዋቾችን ጠርተዋል

ጳግሜ 4 ቀን ከሴራሊዮን አቻው ጋር ሁለተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለሚያደርጉት ዋልያዎች አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ 34 ተጫዋቾችን ጠርተዋል። ዋልያዎቹ የምድብ ጨዋታውን ለማድረግ የሚረዳቸውውን ዝግጅት ከነሀሴ አንድ ጀምሮ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። እነዚህ ተጫዋቾቹ በክረምቱ ዝውውር ከተቀላቀሉት ክለብ ጋር የተጠቀሱ ናቸው። ግብ ጠባቂዎች አቤል ማሞ (መከላከያ) ሳምሶን አሰፋ (ድሬዳዋ ከተማ) ተክለማርያም ሻንቆ (ሀዋሳ ከተማ) ፂዮን መርዕድ (አርባምንጭ ከተማ)…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም መርሃ ግብር ነገ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም መርሃ ግብር ነገው በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል። በነገው እለት ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደው የእርቀ ሰላም መርሃ ግብር በአሜሪካ ከተካሄደው ቀጥሎ የሚካሄድ ሁለተኛው መሆኑም ታውቋል። በእርቀ ሰላም መርሃ ግብሩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የሀይማኖት መሪዎች እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እንደሚታደሙበትም ተገልጿል። በጥቅሉ ሁለተኛው…

በትግራይ ክልል የምህረት አዋጁ የሚመለከታቸው 56 የክስ መዝገቦች ተቋረጡ

የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታን ለማሳደግና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በቅርቡ የጸደቀውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ የ56 የክስ መዝገቦች እንዲቋረጥ መደረጉን የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አረጋይ ገብረእግዚአብሄር፥ በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ የፀደቀውን የምህረት አዋጅ በክልሉ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል ብለዋል። በእዚህም የምህረት አዋጁ የሚመለከታቸው 56 የክስ መዝገቦች ተቋርጠው ተከሳሾች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉን አመልክተዋል፡፡ ካለፈው…

የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት 14 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ

የሐምሌ ወር ሀገራዊ የዋጋ ግሽበት 14 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ መሰረት የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር የ 0 ነጥብ 7 በመቶ ቅናሽ ማስመዝገቡን ጠቁሟል። በሀምሌ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት 16 ነጥብ 7 ሆኖ ሲመዘገብ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ደግሞ የ10 ነጥብ 9 በመቶ…

የአፕል አሴት 1 ትሪሊየን ዶላር ደረሰ

አፕል የ1 ትሪሊየን አሴት ሲያዝመዘግብ በአሜሪካ የህዝብ ኩባንያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ነው ተብሎለታል፡፡ ሆኖም አፕል ትሪሊየን ዶላርን ሲሻገር በዓለም የመጀመሪያው አይደልም የተባለ ሲሆን ከዚህ ቀደም በነዳጅ ዘርፍ ላይ የተሰማራው በአሁኑ ወቅት ዋጋው ያሽቆለቆለበት ፔትሮቻይና ቀዳሚ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የአፕል ኩባንያ እዚህ አሴት ላይ ለመድረስ የበቃው ሐሙስ በዋለው የአክስዮን ሽያጭ ለአንድ አክስዮን ከ207 ነጥብ 04 ዶላር በላይ…

አዲስ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ መከላከያ መድሃኒት ማግኘታቸውን ተማራማሪዎች ገለጹ

አዲስ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ መከላከያ መድሃኒት ማግኘታቸውን ተማራማሪዎች ገለልጸዋል። መድሃኒቱ የሳንባ ነቀርሳ ባክቴሪ ወደ ሰውዎች ሰውነት ከገባ በኋላ ወደ ሳንባ ነቀርሳ በሽታ እንዳይቀየር የሚያደርግ መሆኑ ነው የተገለጸው። በኒውዚላንድ የኦታጎ ዩንቨረሲቲ ተመራማሪዎች ይፋ ያደረጉት ይህ መድሃኒት ለህፃናትም ሆነ ለአዋቂዎች ለ4 ወራት በእየቀኑ በተከታታይ ከተወሰደ በኋላ በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል ነው ተብሏል። በተመሰሳይ መልኩ ቀደም ሲል በሽታውን ለመቆጣጠር…

አዲስ የተሾሙት ስምንት አምባሳደሮች ሰሞኑን ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ

አዲስ የተሾሙት ስምንት አምባሳደሮች ሰሞኑን ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም እንደገለፁት፥ አምባሳደሮቹ የተመደቡባቸው ሀገራት ይሁንታ ከተገኘ በኋላም የተመደቡበት ሀገራት ይፋ ይደረጋል። ቃል አቀባዩ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይ የአምባሳደሮቹ ቃለ መሃላ ለነገ ቀጠሮ የተያዘለት እንደነበር የተገለፀ ቢሆንም፥ በዕለቱ ሌላ ብሄራዊ ሁነት ያለ በመሆኑ…

በሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው። መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ያሰረከበባቸው ተጠርጣሪዎች አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው። የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram