እሰከ ነሃሴ መጨረሻ ድረስ የእርቀ ሰላም ጉባኤ ሊካሄድ ነው

የኢትዮዽያውያን ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ መግባባት ዓለማቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እሰከ ነሃሴ መጨረሻ ድረስ የእርቀ ሰላም ጉባኤ ሊያካሄድ መሆኑን አስታወቀ፡፡ አስተባባሪ ኮሚቴው የእርቀ ሰላምና የመደመር ህዝባዊ ጥሪ ለሚታሰበው ሰላማዊ ትግልም አጠናካሪ ሆኖ አግኝተነዋል ብሏል። በመግለጫውም ለብሄራዊ መግባባትና እርቀ ሰላም ላይ ጽኑ እምነት ያላቸው ሁሉ ኮሚቴው በሚያዘጋጀው እስከ ነሃሴ 2010 መጨረሻ ድረስ ተግባራዊ በሚደረገው ጉባኤ…

Advertisements

ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት አጠናቀው አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ ከመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል። በዚህ ወቅትም ተመድ በኤርትራ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ለዋና ፀሃፊው ይፋዊ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ጥያቄው…

የክልሉ ህዝብ በተለይም ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ መጠበቅ አለበት- አቶ ለማ መገርሳ

የኦሮሚያ ክልል ህዝብ በተለይም ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ እንዲጠብቅ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ አሳሰቡ። በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የጨፌ ኦሮሚያ 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለትም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው። በጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባዔ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳም በክልሉ ባሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ለጨፌው አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በክልሉ ባለው…

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላምና ወዳጅነት ስምምነት መፈራረማቸው ለዜጎቻቸው ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን አሜሪካ ገለፀች

ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት ለመፍታት የደረሱት ስምምነት ለ20 ዓመታት ለነበረው ፍጥጫ ፍፃሜ የሰጠ መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፒዮ አስታወቁ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የፈረሙት ስምምነት ሀገራቱ ዜጎቿቸውን ወደ ብልፅግና፣ ሰላም እና ፖለቲካዊ ለውጦች ለመምራት የሚያስችል እንደሆነም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የገለፁት። ሀገራቱ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል የደረሱት ስምምነት ዜጎቻቸው በሚጋሯቸው…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በ100 ቀናት የኢትዮጵያን ተሰሚነት ከፍ የሚያደርጉ ዲፕሎማሲ ስራዎችን አከናውነዋል- ምሁራን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፉት 100 ቀናት የኢትዮጵያን ተሰሚነት ከፍ የሚያደርጉ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን አከናውነዋል አሉ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያናገራቸው ምሁራን። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የአፍሪካ ቀንድን ቀጠናዊ ውህደት ለማፋጠን እየተጉ መሆኑንም ገልፀዋል። ዶክተር አብይ ጅቡቲን መነሻቸው አድርገው በኬንያ፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ግብፅ እና በቅርቡም በኤርትራ ጉብኝት አድርገዋል። በመካከለኛው ምስራቅም በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚገኙባቸው…

የኤች አይ ቪ ቫይረስ ክትባት የምርምር ውጤት ተስፋ ሰጪ ሆኖ ተገኝቷል- ተማራማሪዎች

የኤች አይ ቪ ቫይረስ ክትባት ላይ አየተደረገ ያለው ምርምር ውጤት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተመራማሪዎች ገለጹ። የቦስተን ተመራማሪዎች እድሜያቸው ለአቅመ ሄዋንና አዳም በደረሱ ጤናማ ሰዎችና ጦጣዎች ላይ በአደረጉት ምርምር ክትባቱ የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ማድረግ ችሏል ነው የተበላው። ጥናቱ ከተካሄደባቸው ጦጣዎች መካከል ሁለት ሶስተኛ ያህሉ ከኤች አይቪ ባይረስ ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው ቫይረሶች መካላከል መቻሉም ነው…

ፌስቡክ በቀጣዩ ዓመት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ ሊያስተላልፍ ነው

ግዙፉ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ በቀጣዩ ዓመት 380ዎቹንም የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በደቡብ ምስራቅ እስያ ለሚገኙ ሀገራት በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ፡፡ ፌስቡክ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ ለማስተላለፍና የብሮድካስት መብት ለማግኘት ከ264 ሚሊየን ዶላር በላይ ማውጣቱ ተገልጿል፡፡ ፕሪምየር ሊጉንም በአራት ሀገሮች በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን፥ ከሀገራቱ መካከልም ታይላንድ፣ ቬትናም ላዖስ እና ኮምቦዲያ ናቸው ተብሏል፡፡ በነዚህ በአራቱ ሀገራት በቀጥታ ፕሪምየር ሊጉን…

ጭንቀትን ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ለማስወገድ

አሁን ላይ ጭንቀት የበርካቶች የዕለት ተዕለት ችግር እየሆነ መምጣቱን የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታል። ከበዛ የስራ ጫና፣ በኑሮ ደስተኛ አለመሆን እና ተያያዥ ምክንያቶች እንዲሁም በማህበራዊ ህይዎት የሚከሰቱ አጋጣሚዎችና በርካታ ምክንያቶች ደግሞ ለዚህ እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ። የጤና እና የስነ ልቦና ባለሙያዎችም ቀለል ባለ መንገድ ከጭንቀት መገላገል የሚችሉበትን መንገድ ይጠቅሳሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ በጭንቀት ጊዜ አድሬናሊን ሰውነት ውስጥ ስለሚበዛ ይህን…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram