‘‘ከኬሞ ቴራፒ’’ በኋላ ጽንስ ለመጸነስ የሚያስችል ሰው ሰራሽ ኦቫሪ ይፋ ሆነ

‘‘ከኬሞቴራፒ’’ በኋላ ጽንስ ለመጸነስ የሚያስችለውን ሰው ሰራሽ ኦቫሪ መስራታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ። የዴኒማርክ ዶክተሮች ከሰዎች እንቁላልና ቲሹ የሰሩት አቮሪ ‘‘ከኬሞቴራፒ’’ እና ሌሎች ከባድ ህክምናዎች በኋላ ለመጸነስ የማይችሉ እናቶችን እንዲጸንሱና ዘራቸውን ለመተካት ያስችላል ተብሏል። የካንሰር ህሙማን እናቶች ላይ የካንሰር ህክምና ከመደረጉ በፊት ኦቫሪያቸውን በማስወገድና ከህክምናው በኋላ እንደገና በመቀጠል እናቶች በተፈጥሯዊ መንገድ እንዲጸንሱ ማድረግ አንደሚቻል ዘገባው አስታውሷል። ይሁን…

Advertisements

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልገሎት ከከተማ አስተዳደሩ የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ድጎማ ጠየቀ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልገሎት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የድጎማ በጀት ጠየቀ። አገልገሎቱ ለባቡር መለዋወጫ እቃዎች ግዥ እና ለሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎች የሚልው ድጎማ ነው ከአስተዳደሩ የጠየቀው። የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የመዲናዋን የትራንስፖርት እጥረት በመቀነስ ረገድ የራሱን ሚና ቢጫወትም እያደገ ከመጣው የመዲናዋ ነዋሪ አንፃር ራሱን ማሻሻል አልቻለም። በኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ ምክንያት…

ደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ዘመን ለማራዘም የሚያስችል የህገ መንግስት ማሻሻያ አዘጋጀች

የደቡብ ሱዳን መንግስት የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን የስልጣን ዘመን ለማርዘም የሚያስችል ረቂቅ የህገ መንግስት ማሻሻያ ማዘጋጀቷ ተሰማ። የሀገሪቱ መንግስት ያቀረበው የህገ መንግስት ማሻሻያ የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ላይ ቆይታ በሶስት ዓመት የሚያራዝም መሆኑም ተነግሯል። የደቡብ ሱዳን ፓርላማም በቀረበለት የህገ መንግስት ማሻሻየ ላይ ክርክር መጀመሩ ታውቋል። የሀገሪቱ የፍትህና የህገ መንግስት ጉዳዮች ሚኒስትር ፓውሊኖ ዋናዊላ ለሀገሪቱ ብሄራዊ የሽግግር ህግ አውጪ…

የቀድሞ የማለዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቀድሞ የማለዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ራዛቅ በሙስና ቅሌት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በነገው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ ሲሆን በሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር የሚተዳደር የልማት ድርጅትን (1MDB) ዘርፈዋል በማለት ነው ክስ የተመሰረተባቸው፡፡ የጸረ ሙስና ኮሚሽኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበር ራዛቅ በኩዋላ ሉምፑር የግል መኖሪያ ቤት ላይ በጸረ ሙስና…

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ግጭት ተፈጠረ

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ከዛሬ ጠዋት (ሰኔ 26) ጀምሮ ግጭት መፈጠሩ ተገለጸ። የግጭቱ ምክንያት የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበትን የእርሻ መሬት እንዳያርሱ በመከልከላቸዉ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ተብሏል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘላለም ልጃለም እንደተናገሩት፤ የእርሻ መሬቱን ለረጅም ዓመታት እየተጠቀሙበት የሚገኙት የኢትዮጵያ አርሶ…

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት አደረጉ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ተገለፀ። ፕሬዚዳንቱ አቡዳቢ ሲደርሱም የአቡዳቢ ልዑልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ወታደራዊ ሀይል አዛዥ ሼህ ሙሀመድ ቢን ዛያድ አል ናህያን አቀባበል አድርገውላቸው። የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንደሚያጠናክረው ተገልጿል። ልዑሉ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በሁለቱ ሀገራት የጋራ በሆኑ ነጥቦች ፣ በአካባቢያዊ እና…

በጋላፊ ቅርንጫፍ ባለው የሲስተም እና መብራት ችግር ለእንግልት መዳራጋቸውን ሹፌሮች ገለፁ

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጋላፊ ቅርንጫፍ ባለው የሲስተም እና መብራት ችግር ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ሽፌሮች ገለፁ። ይህን ቅሬታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡት ሹፌሮች በጁቡቲ መስመር አስር አመት እና ከዛም የሰሩ ናቸው። ሹፌሮቹ ባለፉት ሶስት እና አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጋላፊ ቅርንጫፍ እየጋጠማቸው ያለው ችግር ስራ እና ህይወታቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ይናገራሉ። በቅርንጫፍ ተደጋጋሚ…

ዚምባበዌ በህገ ወጥ መንገድ ከአገር የወጣን 850 ሚሊዮን ዶላር አስመለሰች

ዚምባብዌ በህገወጥ መንገድ በተለያዩ አካላት ወጥቶ የነበረውን ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ አስመለሰች። በዚምባብዌ በህገወጥ መንገድ ከሀገር ከወጣው 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር እስካሁን 850 ሚሊዮን ዶላር ለማስመለስ መቻሉን የአገሪቷ ፕሬዚደንት ምናንጋግዋ አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ ከሀገሪቱ ገንዘብ የወሰዱ አካላት የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ የሶስት ወራት ቀነ ገደብ መስጠታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ የተሰጠው ቀነ ገደቡ ባለፈው መጋቢት ወር ተጠናቋል፤…

ትንሽ ሰው ትንሽ ነው፤ አንሶ ያሳንሳል

“ትንሽ ሰው ትንሽ ነው፤ አንሶ ያሳንሳል” … (ሊያውቁት የሚገባ!) ትንሽ ከፊት ሲሆን አገር ያሳንሳል፡፡ (ፋሲል ደሞዜ) በኩር ጋዜጣ ነጻ አስተያየት በሚሰጥበት አምዱ ይሄን አስተያየት ይዟል፡፡ ሙሉውን አንብቧት ! -አደባባይ የወጣነው ላለፉት 27 ዓመታት በዘር፣ በጎሳና በጎጥ እየለያዩ ሲያጨፉጭፉን፤ አንጡራ ሀብታችንን እየዘረፉ በድህነት ሲያቆራምዱን፣ ጠባብና ትምክህተኛ የሚሉ ተለጣፊ ስያሜዎችን እያደሉ ስነልቦናችንን ሲሸረሽሩ፤ ህፃን፣ እናት፣ ነፍሰጡርና አረጋዊያንን…

የደቡብ ክልል የኮንሶ ባህላዊ መሪ ካላ ገዛህኝ ወልዱን ጨምሮ የ188 ሰዎች ክስ እንዲቋረጥ ወሰነ

በደቡብ ክልል የኮንሶ ባህላዊ መሪ  ካላ ገዛህኝ ወልዱን ጨምሮ የ188 ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሪት ትዛታ ፈቃዱ፥ ክሳቸው የተቋረጠላቸው ሰዎች በክልሉ በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን በኮንሶ ወረዳ ከ2007 እስከ መስከረም 2009 በነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ምክንያት ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ ናቸው ብለዋል። በሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram