ቻይና በ13.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአሉሚኒየም ፋብሪካ ለመገንባት በዝግጅት ላይ ነች

ቻይና በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአሉሚኒየም ፋብሪካ በ13.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኗ ተገልጿል፡፡ ቻይና በኢትዮጵያ ለመገንባት በዝግጅት ላይ ያለችው አዲሱ የአሉሚኒየም ፋብሪካ በአለም ላይ ተመራጪ የሆነ የአሉሚኒየም የቧንቧ መስመር የሚያመርት ነው፡፡ ኩባን ያው በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የንግድ ዘርፍ በአዳዲስ ገበያ ለማስፋፋት አልሞ ነው በኢትዮጵያ አዲስ የአሉሚኒየም ፋብሪካ ለመገንባት ያቀደው፡፡ በሂደት ላይ የሚገኘው ፋብሪካው…

Advertisements

በልብስ ስፌት ማሽን እና ክር በሚስላቸው የስዕል ውጤቶች ዝናን ያተረፈው ሰዓሊ

የ35 ዓመቱ አሩን ኩማር ባጃጂ የተባለው ህዳዊ በልብስ ስፌት ማሽን እና ክር በሚስላቸው የስዕል ውጤቶች እውቅናን እያተረፈ ነው ተብሏል። አሮን ለተከታታይ 23 ዓመታት በልብስ ስፌት ስራ ላይ የቆየ ሲሆን፥ በትምህርት ቤት የነበረውን የስዕል ንድፍ ችሎታ ከልብስ ስፌቱ ጋር በማስተሳሰር የተዋጣለቸው የስዕል ስራዎችን ለመስራት መቻሉ ነው የተገለጸው። ሰዓሊው ከዚህ ቀደም የዘርፉ ስልጠና የሌለውና የልብስ ስፌት ማሽኑን…

የሜክሲኮ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ መፍጠራቸው ተነገረ

የሜክሲኮ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ደስታቸውን በሚገልፁበት ጊዜ መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ መፍጠራቸው ተነግሯል። መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው የሜክሲኮ ብሄራዊ ቡድን የጀርመን አቻውን በዓለም ዋንጫ ጨዋታ መርታቱን ተከትሎ ደጋዊዎች ደስታቸውን በሚገልጹበት ጊዜ ነው። የሜክሲኮ የርእደ መሬት መከታተያ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከሆነ በሜክሲኮ ሲቲ ከተማ የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰው ሰራሽ የተፈጠረ ነው። ይህም ደጋፊዎች የሜክሲኮ ብሄራዊ ቡድን ረጅመን ላይ…

ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ ብራውዘር እየሰራ ነው

ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ መክፈቻ (ብራውዘር) እየሰራ መሆኑ ተነግሯል። አዲሱ የሞዚላ ብራውዘር ፕሮጀክት “ስኮውት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፥ ያለ ምንም የእጅ ንክኪ ተጠቃሚዎች በድምፅ የሚያዙትን ነገሮች ብቻ የሚከፍት ነው ተብሏል። የሞዚላ የድምፅ ብራውዘር ድረ ገፆችን ከመክፈት በዘለለም በድምፅ ትእዛዝ ወደ ላይ እና ወዳ ታች በማድረግ ለማንበብ የሚያችለን መሆኑም ተነግሯል። “ስኮውት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው…

ካስፐርስኪ በአውሮፓ የሚያደርገውን የሳይበር ወንጀል የመከላከል ስራ አቋረጠ

ካስፐርስኪ የተባለው የኮምፒውተር ደህንነት ተቋም ከአውሮፓ ተቋማት ጋር በመሆን የሚያከናውነውን የሳይበር ወንጀል መከላከል ስራ ማቋረጡን አስታውቋል። ኩባንያው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የካስፐርስኪ ሶፍትዌር ተአማኒነት ይጎድለዋል በሚል ያቀረበውን ሞሽን ለመዋቀም መሆኑ ተነግሯል። ካስፐርስኪ ኩባንያ፥ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ያቀረበበት ውንጀላ ከእውነት የራቀ እና የኩባንያውን ክብር የማይመጥን ነው ብሎታል። የአውሮፓ ህብረት ውሳኔውን ያሳለፈው አሜሪካ እና…

በሰውነት ውስጥ ተቀምጦ የጤና መረጃ የሚሰጥ ቴክኖሎጂ ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ

ገመድ አልባ የኤሌከትሮኒክስ መሳረያ በሰዎች አካል ውስጥ በማስቀመጥ የጤና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ መድረሳቸውን ተመራማሪዎቹ ገለጹ። መሳሪያው ሰዎቹ መድሃኒት በሚወስዱበት ወቅት መድሃኒቱ በሰዎች አካል ውስጥ የሚኖረውን ስርጭት፣ መድሃኒቱ የሚያስከትለውን ለውጥ ለመረዳትና ለአዕምሮ የኤሌክትሪክና የብርሃን ምልክቶችን በመስጠት ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል። በዚህም የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደ ሰዎች አካል አንዲገባ በማድረግ በአዲስ መልኩ…

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከሃዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ እና ወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግጭት በተፈጠረባቸው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል አካባቢዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በነገው እለት በሃዋሳና ወላይታ ሶዶ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩ ይሆናል። ከነገ በስቲያ ረቡዕ ደግሞ በወልቂጤ ከተማ በመገኘት ከከተማዋና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ። ውይይቱ በከተሞቹ ባለፉት ቀናት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሚደረግ ነው። ባለፉት ቀናት…

በዓለም ዋንጫው ስዊድን እና ቤልጂየም ድል ቀንቷቸዋል

5ኛ ቀኑን የያዘው የዓለም ዋንጫ ዛሬ የምድብ ስድስት እና ሰባት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ከቀትር በኋላ 9 ሰዓት ላይ በተደረገ የምድብ ስድስት ጨዋታ ስዊድን ደቡብ ኮሪያን አሸንፋለች። በጨዋታው ስዊድኖች በ65ኛው ደቂቃ ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት የቡድኑ አንበል ግራክቪስት አስቆጥሮ አሸናፊ አድርጓቸዋል። በምድብ ሰባት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ጠንካራ ስብስ የያዘው የቤልጂየም ብሄራዊ ቡድን ፓናማን አሸንፏል። ድሪዬስ መርተንስ አንድ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በምክር ቤቱ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ሙሉ ማብራሪያ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ዙሪያ እና ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ኢኮኖሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት በሃገሪቱ በተከሰቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት፥ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተናግረዋል። በዚህ ሳቢያም እድገቱ ወደ አንድ አሃዝ መውረዱን ጠቅሰዋል፤…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram