‹‹እኛ በራችንን ዘግተን ስንቀመጥ በዓለም ላይ ግን መሄጃ ያጣ የገንዘብ ውቅያኖስ አለ›› አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያ

በአሥራት ሥዩም አቶ ኤርሚያስ አመልጋ አክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያን በማቋቋምና በቦርድ አመራር ሥራ አስፈጻሚነት  በመምራት እስከ ቅርብ ጊዜ ድርስ መርተውታል፡፡ በርካቶች አዳዲስ የኢንቨስትመንት ሐሳቦችን በኢትዮጵያ የተገበሩ፣ የፋይናንስ ኢንዲስትሪው ውስጥ ባለአንድ ቅርንጫፍ ባንክ የሚል መነሻም ዘመን ባንክን ያደራጁ እየተባሉም ይጠቀሳሉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት አቶ ኤርሚያስ ያደጉትና አፋቸውን የፈቱት ግብፅ ውስጥ በዓረብኛ ቋንቋ ነው፡፡ ከግብፅ ወደ ኬንያናይሮቢ በማቅናትም የእንግሊዝኛና የስዋህሊ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው ለመናገር ያስቻሏቸውን ጊዜያት በኬንያ አሳልፈዋል፡፡ በታዳጊነታቸው ወቅትም ወደኢትዮጵያ በመመለስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሜሪካ ኢንተርናሽናል ኮሙዩኒቲ ስኩል በማጠናቀቅ፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለአንድዓመት ከተማሩ በኋላ ወደ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው መሥርተው ቆይተዋል፡፡ ከ22 ዓመታት በፊት ዳግመኛ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ፣ በአሜሪካ ዎልስትሪት የካፒታል ገበያ…

Advertisements

በናይጄሪያ በተፈፀመ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 31 ሰዎች ሞቱ

በናይጄሪያ ቦኖ ግዛት በተፈፀመ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ። የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመው የሀገሪቱ ጦር ዋና አዛዥ አካባቢው ሰላም መሆኑን በመጥቀስ ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መጠየቃቸውን ተከትሎ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ነው። በቦኖ ግዛት በምትገኘዋ ዳንቦታ ከተማ በተፈፀመው የእጥፍቶ ጠፊ ጥቃትም በትንሹ 31 ሰዎች ሲሞቱ፤ በርካታ ሰዎች ላይ ደግሞ…

በዓለም ዋንጫው ሜክሲኮ ጀርመንን አሸነፈች

በሩሲያ እየተካሄደ ያለው 21 የዓለም ዋንጫ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው። በዛሬው እለት ተጠባቂ የነበረው ጨዋታ በምድብ ስድስት በተደለደሉት ሜክሲኮ እና ጀርመን መካከል ተካሂዷል። ጨዋታውም በሜክሲኮ 1ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የዓለም ዋንጫን ታነሳለች የሚል ግምት የተሰጣት ጀርመንም የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋን በሽንፈት ጀምራለች። በጨዋታው ላይ ሎዛኖ በ35ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል የሜክሲኮ ብሄራዊ ቡድንን አሸናፊ አድርጋለች። እስካሁን ባለው…

የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ለሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦች የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ በእግር ኳስ ውድድሮች በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ የክልሉ ክለቦች 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ። የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ነጋ አሰፋ እንዳሉት የክልሉ መንግስት የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ ከፍተኛ ሊግና ብሄራዊ ሊግ በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ ክለቦች ነው። በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያ ፕርሜየር ሊግ በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ…

ዩጋንዳ ሀምሳ አንድ ኪ.ሜ አውራ ጎዳና (ቀለበት መንገድ) ግንባታ አስመረቀች

ርዕሰ ከተማዋን ካምፓላ ከሀገሪቱ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ጋር የሚያገናኘው መንገድ መሪው ዮሪ ሞሶቮኒ እና የቻይና ባለስልጣን በታደሙበት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡ ከካምፓላ ኢንቴቤ ለሰአታት ይፈጅ የነበረውን ጉዞ ወደ ሰላሳ ደቂቃ ያሳጥራልም ተብሎለታል፡፡ የመንገዱ ግንባታ የተጠናከረ የቻይና እና አፍሪካ ድጋፍ ውጤት ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ሞሶቮኒ ተናግረዋል፡፡ ሶስተኛ የቻይና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዋንግ ያንግ በበኩላቸው ሁሉንም ሀገሮች…

ጣልያን አልቀበልም ያለቻቸው ስደተኞች ስፔን ደረሱ

በነብስ አድን መርከብ ተጭነው በሜዲትሪያን ባህር ላይ ከጣልያንና ማላላ የተገፉ ከ6መቶ በላይ ስደተኞች በስፔን ቫሌንሲያ ወደብ ላይ ደርሰዋል። የስፔን መንግስት ለስደተኞቹ ነጻ የጤና አገልግሎት እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ለያንዳንዱ የጥገኝነት ጉዳይ ግን ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት ጣልያንና ማላላ አንቀበልም ያሏቸው ስደተኞችን እንደሚቀበሉ የስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ስደተኞችን በጫነችው አኳሪየስ በተባለች መርከብ ውስጥ…

ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የራያ ዩንቨርስቲን መርቀው ከፈቱ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የራያ ዩንቨርስቲን በዛሬው እለት መርቀው ከፍተዋል። ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል እና ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ጋር በመሆን ነው ዩኒቨርሲቲውን መርቀው የከፈቱት። በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን ማይጨው ከተማ በመገኘት ዩኒቨርሲቲውን መርቀው የከፈቱት ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክትም አስተላልፈዋል።…

በሞስኮ ብዙ ሰዎች ወዳሉበት ቦታ ጥሶ የገባ ታክሲ የዓለም ዋንጫ ደጋፊዎችን ጨምሮ 7 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

በሩሲያ ሞስኮ ህዝብ ወደ በብዛት ወደተሰበሰበበት ስርፋ ጥሶ የገባ አንድ ታክሲ የዓለም ዋንጫን ለማየት ወደ ሀገሪቱ የገቡትን የውጭ ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ 7 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል። አደጋው የደረሰው በትናንትናው እለት ሲሆን፥ በሞስኮ ቀይ መስቀል አደባባይ በሚባል አካባቢ መድረሱን ነው የዓይን እማኞች የተናገሩት። በአደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥም ሁለቱ የሜክሲኮ ዜግነት ያላቸው ሲሆን፥ በዓለም ዋንጫው…

በአለም ዋንጫ ፈረንሳይ ስታሸንፍ አርጀንቲና አቻ ተለያየች

ዛሬ በተካሄደው የሩሲያው የአለም ዋንጫ በምድብ ሶስት ፈረንሳይ አውስትራሊያን ስታሸንፍ አርጀንቲና ባልተጠበቀ ሁኔታ ከአይስላንድ ጋር አቻ ተለይታለች። ፈረንሳይን አሸናፊ ያደረጉትን ግቦች አንቶኒዮ ግሬዝማን በ58ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት እና ፖል ቦግባ 80ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር የአውስትራሊያን ግብ ጄዲኒካ በ62ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል። ይህን ውጤት ተከትሎም ፈረንሳይ ምድብ ሶስትን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች። በምድብ አራት አርጀንቲና ከአይስላንድ…

ምን ያህሎቻችን ስለ ‹ይባብ ቤተመንግስት› እናውቃለን?

የአማራ ክልል ደራስያን ማህበርና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በይልማና ዴንሳ ወረዳ ደብረ ማይ ቀበሌ የሚገኘውን ይባብ ቤተመነግስት ጎብኝተዋል። ይባብ ቤተ መንግስት በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ ላይ በአፄ ሱስንዮስ እንደተመሰረተ ታሪክ ያስረዳል። ቤተ መንግስቱ ከደንቀዝ ቤተ መንግስት ቀጥሎ ከጎንደር ቤተመንግስት ቀደም ብሎ የታነፀ ነው። በኢትዮጵያ ቀደምት ነገስታት ታላላቅ ጉባኤዎች ተካሂዶበታል። ደም አፋሳሽ ጦርነቶችንም እንዳስተናገደ በታሪክ ሰፍሮ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram