ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች 3 ቢሊየን ዶላር መጠን ያላቸው የውጭ ምንዛሬ ድጋፍና ኢንቨስትመንት ስምምንቶችን ተፈራረሙ

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዑል አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ አዲስ አበባ ገብተዋል። የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለልዑል አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን፥ የቦሌ ለሚ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ግንባታ የሚገኝበትን ደረጃ በጋራ ጎብኝተዋል። በመቀጠልም በብሄራዊ ቤተመንግስት ውይይት አድርገዋል።…

Advertisements

ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንመልሳለን – ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ክልል ያለአግባብ የተፈናቀሉ በክልሉ ሲኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰሩ ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ለማ ተፈናቃዮቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ነበሩበት ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ቦታ ላይ ሰላም ቢሰፍንም በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችን ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉ ገልጸው፥ ህዝቡ ከመንግስት ጋር በመተባበር ሰላሙን እንዲያስጠብቅ ጥሪ…

የዓለም ባለትልቅ እግሩ ቬንዙዌላዊ አዲስ ጫማ ሰሪ ከጀርመን አግኝቷል

ቬንዙዌላዊው ጄሰን ኦርላንዶ ሮድሪጌዝ ሄርናንዴዝ በእግሩ ትልቀት የዓለምን ክብረ ወሰን የያዘ መሆኑ ይታወሳል። ባለ ትልቅ እግሩ ኦርላንዶ ሮድሪጌዝ ሄርናንዴዝ የእግሩ ትልቀት በዓለም ታዋቂ ቢያደርገውም፤ ጫማ ማግኘት ግን ለእሱ በጣም ፈታኝ ነገር እንደሆነበት ነው የሚናገረው። የወጣቱ ክብረ ወሰኑን በያዘበት ወቅት የቀኝ እግረ 40 ነጥብ 1 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ሲሆን፥ የግራ እግሩ ደግሞ 39 ነጥብ 6 ሴንቲ…

የአለም ዋንጫ እንግዶችን ለመቀበል ፈገግታን መማር ግድ የሆነባቸው ሩሲያውያን

ሩሲያውያን የአለም ዋንጫን ለመታደም ወደ ሀገሪቱ የሚያቀኑ እንግዶችን በወዳጅነት መቀበል እንዲችሉ የሳቅና ፈገግታ ጥበብን መሰልጠናቸው ተነግሯል። ሩሲያ በአለም ፊታቸው ላይ የሳቅ ወይም የፈገግታ ስሜትን ከማያሳዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይመደባሉ። በዚህ ምክንያት ከተለያዩ ዓለም ሀገራት ወደ ሩሲያ የሚያቀኑ ሰዎች ሩሲያውያን በወዳጅነት የማይቀርቡ ብለው የሚገልጿቸው በመሆኑ አመለካከቱን ለመቀየር ይህ የሳቅ እና ፈገግታ ጥበብ ስልጠና እንደተሰጣቸው ተገልጿል። በሩሲያ አዘጋጅነት…

የአለም ዋንጫን ተከትሎ የተጫዋችን ምስል በፀጉር ላይ የሚነቅሰው ፀጉር አስተካካይ

በሩሲያ ሚካሄደውን አለም ዋንጫ ተከትሎ ተመልካቾች በሚወዷቸው ተጫዋቾች ምስል ቅርፅ ወይም ንቅሳት ፀጉራቸውን ማሳመር የሚችል ባለሙያ ከወደ ሰርቢያ ብቅ ብሏል፡፡ ማሪዎ ሀቫላ ተባለው ፀጉር አስተካካይ የሜሲ እና ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ምስሎችን በአድናቂዎቻቸው የእራስ ቅል ጀርባ እየነቀሰ እንደሚያሳምር ተነግሯል፡፡ ፀጉር አስተካካዩ ከእግር ኳስ ተጫዋቾች ምስል በተጨማሪ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሌሎች ፖለቲከኞች ምስል ይነቅሳል…

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዑል አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዑል አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለልዑል አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብዣ አዲስ አበባ የመጡት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናኸያን ለክብራቸው ሃያ አንድ ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።…

ኮሎኔል ክብሮም ገብረማርያም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ኮሎኔል ክብሮም ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ኮሎኔል ክብሮም የአየር ሀይል ሎጂስቲክስ ሀላፊ፣ ቀጥሎም የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አዛዥና የዩንቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል። ከዚያ ቀደም ብሎ ኮሎኔል ክብሮም አስከፊውን የደርግ ስርዓት ለመገርሰስ ሲካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ግንቦት ወር 1968 ዓ.ም ተቀላቅለዋል። በዚህም የትጥቅ ትግል ተሰልፈው የተሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት ሲፈፅሙ የነበሩት ኮሎኔል ክብሮም፥ በነበራቸው ብቃት 1975…

መንግስት ከ300 ለሚበልጡ የፌደራል የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የኢፌዴሪ መንግስት ከ300 ለሚበልጡ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 289 የሚሆኑት በሽብር ወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸው ናቸው። ዛሬ በይቅርታ እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው መካከል ዘጠኙ የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው የነበሩ ሲሆን፥ ሦስቱ በልዩ ልዩ ወንጀሎች እንዲሁም ሦስቱ ደግሞ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው ተብሏል። ይቅርታ ከተደረገላቸው አብዛኛዎቹ ታራሚዎች…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram