የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተዳደሪያ እና መቋቋሚያ አዋጅ እየተሻሻለ ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተዳደሪያ እና መቋቋሚያ አዋጅ እየተሻሻለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በኢትዮጵያ በመንግስት የሚተዳደሩ ከ40 በላይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይገኛሉ። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በቁጥር ይህን ያህል በዝተው ተደራሽ ለመሆን ቢሞክሩም፥ ትውልድ ከመቅረጽና የተቋቋሙበትን አላማ ከማሳካት አንጻር ግን ችግር እንደሚስተዋልባቸው ይነገራል። በተቋማቱ የሚስተዋለው ችግርም እየታየ ላለው የትምህርት ጥራት ችግር መንስኤ መሆኑን ነው አስተያየት ሰጭዎቹ የሚናገሩት።…

ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

I. መግቢያ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 3 አስከ 5 ያካሄደዉን አስቸኳይ ሰብሰባ አጠናቋል። ህወሓት/ኢህአዴግ በ17 ዓመቱ የትጥቅ ትግልም ሆነ ሩብ ክፍለ ዘመን ባስቆጠረው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ትግል ምዕራፎች ሁሉ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረግነው ትግል በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፍን እዚህ ላይ መድረስ ችለናል። የ43 ዓመታት የድልና የፅናት ጉዟችን ስኬት ምንጭ የጠራና ብቁ አብዮታዊ መስመር ይዘን…

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጅ ተቋም ተማሪዎች ንብረት ከማውደም እንዲቆጠቡ ዩኒቨርሲቲው አሳሰበ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ በማቅረብ በዩኒቨርሲቲው ንብረት ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀረበ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አራጋው ብዙዓለም እንዳሉት፥ ተማሪዎቹ አሁን ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሆነዋል። ጉዳዩን በግቢ ፖሊሶች መቆጣጠር አልተቻለም ያሉት አቶ አራጋው፥ ሁኔታውን ለማረጋጋት የአድማ በታኝ ፖሊስ ወደ ግቢው መግባቱን ተናግረዋል። አሁን ላይም ተማሪዎች በየመኖሪያ ክፍሎቻቸው እንዲገቡ…

ጀምበር፡ ከሰው የተለየ ኃይል ያለው ኢትዮጵያዊው ወጣት

የ28 ዓመቱ ብስራት ደበበ የምህንድስና ምሩቅ ሲሆን ኮኔክትከት በተሰኘችው የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ነዋሪ ነው። በአሁን ሰዓት ኤንጅን በሚያመርት ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ እየሠራ ይገኛል። ብስራት ኢትዮጵያን ለቆ ሲውጣ የ14 ዓመት ወጣት ቢሆንም እስካሁን ባህሉ፣ ኃይማኖቱና የዕጣኑ ሽታ ከአዕምሮው እንዳልወጣ ይናገራል። እነሆ አሁን በአሜሪካ ባደገበትም ጊዜ የተዋወቀው የጥበብ ስልት ብስራት ላይ የተለየ ተፅዕኖ አሳድሮበታል። ብስራት ተቀጥሮ ይስራ…

በሲዳማ የዘመን አቆጣጠር 2011 ጀመረ

የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምበላላ በዓል ዛሬ በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ በደማቅ ሥነ-ሥርዓቶች ተከብሯል። ከሁሉም የሲዳማ ዞን ወረዳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ተወላጆች እንዲሁም የተለያዩ ቱሪስቶች በዓሉን ታድመዋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የአካባቢው ተወላጅ እና ጋዜጠኛ አለሙ አመዬ፤ ”ይህ የዘመን አቆጣጠረር የሲዳማ ብሄረሰብ የፀሃይ፣ የጨረቃ እና የከዋክብት የተፈጥሮ ኡደትን እያሰላ ዘመን የሚቆጥርበት ጥበብ ነው”ይላል። የሃገር ሽማግሌዎች ”አያንቱዎች”…

“አሁን ያለው የፌደራሊዝም ሥርዓት የአማራውን ህዝባዊ አንድነት የሚገረስስ ሆኖ ነው ያገኘነው”

ላለፉት ቀናት የመስራች ጉባዔውን በባህር ዳር ከተማ ሲያከናውን የቆየው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ፤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን በመምረጥ ተጠናቅቋል። በዚህም መሠረት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን የፓርቲ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ክርስቲያን ታደለን በፓርቲው ምስረታ፥ ቀጣይ እርምጃዎች እንዲሁም በተነሱ ትችቶች ዙሪያ ቢቢሲ አነጋግሯቸዋል። ቢቢሲ- በቅርቡ መስራች ጉባኤያችሁን…

ሶፊያ ከዐብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች

ቅንድቦቿ ሲንቀሳቀሱ፣ የዓይን ሽፋሽፍቷ ሲርገበገብ፣ በቀለም የተዋበው ከንፈሯ ለንግግር ሲንቀሳቀስ፣ ጥርሶቿ ገለጥ ሲሉ በእርግጥ ይህች ሴት ሰው ሠራሽ ናት? ያስብላል። ሶፊያ እምነት ታሳጣለች፤ ከራስ ጋር ታጣላለች። ጋዜጠኞች በእንግድነት ጋብዘዋታል፤ ዝናዋ በዓለም ናኝቷል፤ እንደሶፊያ ትኩረት የሳበ ሮቦት ገና አልተወለደም። አሜሪካዊውን ተዋናይ፣ የፊልም አዘጋጅ፣ ራፐርና የሙዚቃ ጸሐፊ ዊል ስሚዝን ጨምሮ ታዋቂ የፊልም ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም ግብዣ አድርገውላት…

በጃንጥላ ተከልሎ ቀዶ ህክምና? በችግር የተተበተበው ፈለገ ህይወት ሆስፒታል

በቅርቡ የባሕር ዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ፎቶግራፍን በማህበራዊ ድረ ገጾች ያዪ ሰዎች ጥያቄ ነው። የቀዶ ህክምና ክፍሉ ጣሪያ ቀዳዳ ኖሯል። በጣሪያው ሽንቁርም ዝናብ ይገባል። ሀኪሞች ቀዶ ህክምና ሲያደርጉ ዝናብ እንዳያውካቸው በጃንጥላ ይከላከላሉ። ነፍሳቸውን በሀኪሞቹ እጅ ጥለው አልጋው ላይ ያሉ ታካሚዎችም በጥላው ይጋረዳሉ። ነገሩን በፎቶግራፍ መመልከትና ቦታው ሆኖ የሁነቱ አካል መሆን ይለያያሉ።…

የአቢሲኒያ ባንክ የዝርፊያ ድራማ

ለአቶ አንተነህ ረዳኢ ትናንት አመሻሽ ልክ እንደወትሮው ሁሉ የተለመደ ምሸት ነበር። ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሻይ ቡና ለማለት ቦሌ መድሀኒያለም ጀርባ በሚገኘው አቢሲኒያ ኮፊ ፊት ለፊት የያዙትን መኪና አቁመው የሚጠጡትን ይዘው መጫወት ጀመሩ። ይህን ጊዜ አንድ ቪትዝ መኪና መጥታ ከእነርሱ መኪና ጋር በኃይል ተላተመች። ግጭቱን ያደረሰው መኪና ለማምለጥ ሲሞክር ተሯሩጠው ለማስቆም ይሞክራሉ። በአቅራቢያውም ፓርኪን የሚሰራ ልጅ…

በወልቂጤ በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን የጉራጌ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ

በወልቂጤ ከተማ በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የጉራጌ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈቱ ሰማን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በተፈጠረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። ከዚህ በተጨማሪም በግጭቱ በሰባት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱንም ተናግረዋል። በግጭቱ ሳቢያም በርካታ የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች መቃጠላቸውን እና ንብረት መውደሙንም ነው የተናገሩት።…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram