ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የመገበያያ ገንዘባቸውን ሊቀይሩ ነው

የሶማሊያ መንግስት አሁን በስራ ላይ ያለውን የሀገሪቱን ገንዘብ በመቀየር አዲስ መገበያያ ገንዘብ ሊያትም መሆኑን አስታወቀ፡፡ ‹‹ሺሊንግ›› በሚል የሚጠራው የሶማሊያ ገንዘብ ባለ5 ሺህ እና 10 ሺህ አዲስ የገንዘብ ኖቶች በሀገሪቱ መንግስት ይፋ ተደርገዋል፡፡ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ባለ1 ሺህ የብር ኖት በአዲሶቹ የገንዘብ መገበያያ እንደተካተተ ተጠቁሟል፡፡ አዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች በሀገሪቱ በአብዛኛው ገበያ ውስጥ…

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ታዳጊ መሃመድ አብዱልዓዚዝን እና አበጠር ወርቁን ጎበኙ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለረጅም አመታት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ታዳጊ መሃመድ አብዱልዓዚዝን እና ጥቃት የተፈጸመበትን ታዳጊ አበጠር ወርቁን ጎበኙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብጽ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በመገኘት ሁለቱን ታዳጊዎች ዛሬ ማምሻውን ጎብኝተዋቸዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም መንግስት ለታዳጊዎቹ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታዳጊዎቹን ወላጆች ስጋት አይግባችሁ በማለት መንግስት…

የባህርዳር ከነማ እና የደሴ ከተማ ጨዋታ ተቋረጠ

ባሕር ዳር፡ሰኔ 04/2010 ዓ/ም(አብመድ) በዛሬው ዕለት ባህርዳር ከነማ እና ደሴ ከተማ ደሴ ላይ ባደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታ እስከ እረፍት ባለው ባህርዳር ከነማ 1 ለ 0 እየመራ ቆይቷል፡፡ ከዕረፍት መልስ ግን ዳኛው ደህንነት አልተሰማኝም ጨዋታውም በሰላም ይጠናቀቃል ብዬ አላስብም በማለቱ ምክንያት የጸጥታ ሃይሉ ከሁለቱ የክለብ አመራሮች ጋር በመሆን ለሌላ ጊዜ የስፖርት ፌዴሬሽኑ ባወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት…

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በአማርኛ የሠጡት የካይሮ መግለጫ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሀገራችን መሪዎች ባልተለመደ መልኩ በካይሮ መግለጫ የሠጡት በአማርኛ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን በሀገሪቱ የስራ ቋንቋ ማስተላለፋቸውን እንዴት ታዩታላችሁ? ለሌሎች መሪዎች የሚኖረው አስተምህሮ ምንድን ነው? ለቋንቋው እድገትስ? ሃሳባችሁን አካፍሉን ፡፡

በአሸባሪዎች በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አጽም ወደ አገራቸው እንዲመጣ ስምምነት ተደርሷል

በሊቢያ በስደት እያሉ በአሸባሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያንን አጽም ከተቀበረበት በማውጣት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ የመጨረሻ እረፍት እንዲያገኝ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደረሰ። በግብፅ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት ትኩረት ሰጥተው ካነሱት ሃሳብ መካከል የዜጎች ከእስር መለቀቅና በአሸባሪዎች በግፍ የተገደሉት አጽማቸው በአገራቸው በክብር እንዲያርፍ…

ዚምባቡዌ ስሟን በአለም ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ አሰፈረች

ዚምባቡዌ ማሪምባ በተባለው የባህል ሙዚቃ መሳሪያ 222 የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ተማሪዎችን በማሳተፍ ቀዳሚ ሃገር መሆኗን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ አምስት ደቂቃ ርዝማኔ በነበረው በዚህ የህብረት ሙዚቃ ጨዋታ የሃገሪቱን ማሃንጋ ካቱፒራ የተሰኘውን ታዋቂ ዜማ በመጫወት ክብረ ወሰን መስበር ተችሏል፡፡ እኤአ በ2016 አውስትራሊያ 108 ተሳታፊዎችን ባካተተው የጋራ የሙዚቃ ቅንብር በአለም ክብረ ወሰን ስሟን አስመዝግባ ቆይታለች ፡፡ አሁን ዚምባቡዌ በ…

የለውጥ መሪው ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ-በዓለም አቀፉ ዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት እይታ

የለውጥ መሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዓለም አቀፉ ዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት እይታ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ በተሰኘው አምዱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን በተመለከተ እና በአጭር ጊዜያት ውስጥ ስላከናወኗቸው ተግባራት ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዞ ወጥቷል፡፡ እንደ መጽሄቱ ትንታኔ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከወራት በፊት ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መጥተዋል፡፡ የአስቸኳይ…

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ እና በትግርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ እና በትግርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው

የአክሱም ዩኒቨርስቲ በግዕዝ ቋንቋ እና በትግርኛ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ የትምህርት መርሃ ግብሩን የሚጀምረው በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን መሆኑን አስታውቋል፡፡   መርሃ ግብሩ በመጀመሪያ ዲግሪ ለሦስት ዓመታት የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡ በቀጣይም ሁለተኛ ዲግሪ ለመጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርስቲው የመርሃ ግብሩ መጀመር በአክሱም ከተማና ዙሪያ ለሚገኙ ታሪካዊ ምርምሮችና ጽሁፎች በቀላሉ ለመተርጎምና ጥቅም ላይ ለማዋል…

በዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን ድል ቀናቸው

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስዊድን ስቶኮልም ላይ ባካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አሸንፈዋል፡፡ በሴቶች በተደረገው የ1500 ሜትር ውድድር ጉዳፍ ጸጋዬ 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ64 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አንደኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ በወንዶች በተደረገው የ5000 ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ 13 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ ከ5 ማይክሮሰከንድ በመግባት አሸንፏል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ አባዲ አዲስ 13 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ…

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ የተካሄዱ ሲሆን፥ ጧት 4፡00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገናኙት መቐለ ከተማ እና ፋሲል ከተማ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ሁለተኛው ጨዋታ 9፡00 ሰዓት ላይ የተካሄደ ሲሆን፥ ኤሌክትሪክ ከሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡ አዲግራት ላይ ወልዋሎ ደደቢትን ሀዋሳ ላይ ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማን…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram