ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የኡጋንዳ ከፍተኛ ሜዳሊያ ተሸለሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የኡጋንዳ ከፍተኛ ሜዳሊያ ተሸለሙ። በኡጋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በተከበረው የሀገሪቱ 29ኛው ብሄራዊ የጀግኖች በዓል ታድመዋል። በዚህ ብሄራዊ በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአፍሪካ እና ለኡጋንዳ መልካም ስራ ለሰሩ ሰዎች ሀገሪቱ የምታበረክተውን ሜዳሊያ ከፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ…

ፈረንሳይ የኢትዮ-ኤርትራን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ትደግፋለች – የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የነበረውን አለመግባባት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት በምታደርገው እንቅስቃሴ ፈረንሳይ ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን ይቬስ ሊ ድሪያን ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዥያን ይቭስ ለድርየን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዥያንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የኢትዮጵያ…

2 ሺህ 38 ግራም የሚመዝን ሜርኩሪ በመቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ

በመቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ 2 ሺህ 38 ግራም የሚመዝን ሜርኩሪ መያዙ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጲያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የትምህርትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም መኮንን ለፋናብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ሜርኩሪው በህገወጥ መንገድ በአውሮፕላን ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ሊጓጓዝ ሲል በተደረገ ፍተሻ ነው የተያዘው። በአሁኑ ሰዓት የተያዘው ሜርኩሪ የማዕድን ነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር እንዲረከብ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡ ትክክለኛ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram