“የሚያዋስነን መረብ ወንዝ ነው፣ ከመረብ ምላሽ የኛ ቦታ ነው” የባድመ አስተዳዳሪ

ወደ መቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ያለቁበት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ቁርሾን ይሽራል ተብሎ የተገመተው የአልጀርስ ስምምነት የነገሮችን ውል አጥፍቶ ለባሰ መቆራቆዝ ሰበብ ሆኖ ቆይቷል። በአልጀርስ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ያልተስማሙትን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይቀይራል የተባለለት ውሳኔ ግን ከሰሞኑ ተሰምቷል። የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል።…

ተማሪዎች ሞባይሎቻቸውን ሊነጠቁ ነው

የፈረንሳይ ሕግ አውጪ ምክር ቤት የተንቀሳቃሽ ስልክን በትምህርት ቤቶች ውስጥ መጠቀመን የሚያግድ ረቂቅ አጸደቀ። መንግሥት አዲሱ ሕግ ተማሪዎች ትኩረታቸውን ትምህርት ላይ እንዲደርጉ ያበረታታል ብሎ ያምናል። በተጨማሪም ረቂቁ “የኢንተርኔት ጉልቤዎችን” (cyber bullying) ተማሪዎች ላይ የሚያደርሱትን ዕለታዊ ጥቃት ያስቀራል ተብሏል። ይህ ብቻ ሳይሆን የልቅ ወሲብ ፊልሞችን በስልኮቻቸው እያጮለቁ የሚመለከቱ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችንም አደብ ያሲዛል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።…

“ኤርትራ የምትሰጠው አዲስ መግለጫ የለም” በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር

ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን ከገለጸች ጀምሮ ከኤርትራ መንግሥት በኩል የሚሰጥ ምላሽ ሲጠበቅ ቆይቷል። ሆኖም ፕሬዚዳንቱም ሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ የማነ ገብረመስቀል ዛሬ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ”ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት አቋማችን ግልፅ ነው” ከማለት ውጪ ምንም አይነት ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም። ነገር ግን ቢቢሲ የትግርኛው…

“መንግሥት እየተባባሰ ካለው ብሔርን መሰረት ካደረገ ጥቃት ዜጎቹን ይጠብቅ” አምነስቲ

የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ብሔርን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከመፈናቀል አፋፍ ላይ ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላትን ለመጠበቅ ጣልቃ እንዲገባ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት እንደጠቀሰው በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ሰዮ ወረዳ በዚህ ሳምንት በቡድን የተሰባሰቡ የአካባቢው ወጣቶች የአማሮችን ቤት መክበብ፣ ድብደባና የንብረት ዝርፊያ ፈፅመዋል ሲል ይከሳል። በተጨማሪም ከጥቅምት ወር አንስቶ ቢያንስ…

በሊቢያ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ 6 ግለሰቦች ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕቀብ ጣለ

በድርጅቱ የፀጥታው ምክር ቤት ሰዎችን በህገወጥ መንገድ በማዘዋወር ቀንደኛ በሆኑት ግለሰቦች ላይ የጣለው ማዕቀብ በአለም አቀፍ ደረጃ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ የሚያደርግ ነው፡፡ ማዕቀቡ ከተጣባለቸው መካከል የአገሪቱ የባህር ጠረፍ ጥበቃ ኃላፊ የሆነውን ግለሰብ ጨምሮ አራቱ ሊቢያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ኤርትራዊያን ናቸው ፡፡ የህገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ በሊቢያ ያለውን አለመረጋጋት በመጠቀም በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ…

ፌስቡክ የግል መረጃ አያያዝን ለማጠናከር በሚያደርገው ማሻሻያ 14 ሚሊዮን ደንበኞች ተጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ

ፌስቡክ የደንበኞቹን የግል መረጃ አያያዝን ለማጠናከር ሲባል በሚያከናውናቸው የማሻሻያ ስራዎች ምክንያት 14 ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከእነርሱ እውቅና ውጪ የግል መረጃዎቻቸው በሌላ ሰዎች ሊታይ እንደሚችል ተገለጸ፡፡ አሁን በሚደረገው ማሻሻያ መሰረት ደንበኛው ከዚህ በፊት የግል መረጃውን ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ማካፈል እንዲችል ማስተካከያ ቢያደርግም አሁን በሚፈጠረው ችግር ማንኛውም ሰው መረጃውን ማግኘት እንደሚችል ነው ፌስቡክ ኩባኒያ ያስታወቀው፡፡ የፌስቡክ የግል…

ሰፊ ቅንድቧ ታዋቂ የፋሽን ብሎገር ያደረጋት ወጣት

አብዛኞቹ ቆነጃጂቶች በውበታቸው ላይ ውበት ለመጨመር በተፈጥሮ ያገኙት የቅንድብ ጸጉራቸውን ሲቀንሱ ይስተዋላል። ይሁን እንጂ አንዝሀሊካ ፕሮቶድያኮኖቫ የተባለቸው ሩሲያዊት ወጣት የቅንድብ ጸጉር ግንባሯን በከፊል የሚሸፍን ሲሆን፥ ከዚህ የበለጠ የማሳደግ ፍላጎት አላት ተብሏል። ይህችው ወጣት በተፈጥሮ የታደለችው ሰፊ የቅንድብ ጸጉር የፋሽን ብሎገር ለመሆን እንዳስቻላትም ነው የተገለጸው። በዚህም ወጣቷ ከ90ሺህ በላይ የኢንስታግራምና 10 ሺህ ያህል የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ…

የቻይናው ዜድቲኢ በአሜሪካ የተጣለበትን የ1 ቢሊየን ዶላር ቅጣት ሊከፍል ነው

የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ዜድቲኢ በዩናይትድ ስቴትስ የተጣለበትን የአንድ ቢሊየን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ከሀገሪቱ ጋር መስማማቱ ተገለጸ፡፡ ኩባንያው ላይ ቅጣቱ ሊጣል የቻለው ሀገሪቷ ማዕቀብ ከጣለችባቸው ከኢራንና ሰሜንኮሪያ ጋር የንግድ ልውውጥ አድርጓል በሚል መሆኑ ተነግሯል፡፡ ኩባንያው ወደ ገበያ ከመግባቱ በፊት እንደ ማስያዣ ወይንም መንግስት ያስቀመጣቸው ቅድመሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ እንዲሁም ሁለቱ የገቡት ስምምነት ቢጣስ በሚል 400…

ኦስትሪያ ሰባት መስጊዶችን ልትዘጋ መሆኑን አስታወቀች

ኦስትሪያ በውጭ ሃገራት የሚደጎሙ ሰባት መስጊዶችን ልትዘጋ መሆኑን አስታወቀች። የኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ በተለያዩ ሃገራት ይደጎማሉ የተባሉ ሰባት መስጊዶች እንደሚዘጉ ተናግረዋል። የአሁኑ የመንግስት አቋም መስጊዶቹ ከእምነት አገልግሎት ይልቅ ፖለቲካዊ ተልዕኮን ያነገቡ ናቸው በሚል የተወሰነ መሆኑም ተገልጿል። አንዳንዶቹ መስጊዶች ከቱርክ ብሄርተኝነት አቀንቃኞች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተደርሶበታልም ነው የተባለው። ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram