ጄኔራል አደም መሐመድ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጄኔራል አደም መሐመድን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾሙ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጄኔራል አደም ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲሾሙ የአላቸውን ልምድ ከግምት ውስጥ መግባቱን አመልክቷል። ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ወታደራዊ ማዕረጎችን በሰጡበት ወቅት ለሌ/ጀኔራል አደም መሐመድ…

የግንቦት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13 ነጥብ 7 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ

በግንቦት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13 ነጥብ 7 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ መሰረት የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር ተመሳሳይ ሆኖ ተመዝግቧል። የግንቦት ወር ምግብ ዋጋ ግሽበት 14 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ ሲመዘገብ፤ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ ደግሞ ወደ 12 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።…

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበረች ጀልባ ሰጥማ 46 ኢትዮጵያውያን ሞቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያውያን ስደተኖችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የተመድ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንዳስታወቀው ጀልባዋ ረቡዕ ጧት በኤደን ባህረ ሰላጤ አካባቢ የሰጠመች ሲሆን፥ ጀልባዋ ላይ ከነበሩት ውስጥ የ46 ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉ ነው የተገለጸው። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትም 37 ወንዶች እና  9 ሴቶች ሲሆኑ፥16 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም። ከቦሳሶ ወደብ የተነሳችው ጀልባዋ 100 ያህል ስደተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ስታመራ የነበር መሆኑን የነፍስ አድን ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ገልጸዋል። ተጨናንቀው የተጫኑት…

ጠቅላይ ሚንስቴር አቢይ አህመድ ”የኢኮኖሚ አሻጥር እየተደረገብኝ ነው” አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የእሳቸውን ወደ ስልጣን መምጣት በመቃወም “የኢኮኖሚ አሻጥር/የኢኮኖሚ sabotage/” እየተፈፀመባቸው መሆኑን አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት “ዝርፊያ”ሲሉ በገለፁት ሀገር-አቀፍ የፀረ-ሙስና ጉባኤ ላይ ባደረጉት የ20 ደቂቃ ንግግር ነበር።

ባለ ሁለት ገፅ ስክሪን ላፕቶፕ ይፋ ተደረገ

ኢንቴል ኩባንያ ከዚህ ቀደም ከነበረውና ከተለመደው ላፕቶፕ በተለየ ሁኔታ ኪቦርድን በማስቀረት ባለ ሁለት ገፅ ስክሪን አዘጋጅቶ ይፋ አድርጓል። ይህ ቀላል ላፕቶፕ ታጥፈው የሚገጠሙት ሁለቱም አካላቶቹ ስክሪን ሲሆኑ፥ የወረቀት ማስታወሻን የመሰለ የኤሌክትሮኒክ የተገጠመላቸው መሆኑ ተነግሯል። አዲሱ ባለ ጥምር ስክሪን ላፕቶፕ ያለው የማስታወሻ ደብተር መሳይ አካል በጣም ስስ እና ከጥጥ ከሚዘጋጀው ሞሌስኪኔ ማስታወሻ ደብተር ጋር ይመሳሰላል ተብሏል።…

ሱዳን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ወታደራዊ ግንኙነት ማቋረጧን ገለጸች

ሱዳን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን ወታደራዊ ግንኙነት ማቋረጧን ገለጸች። የሱዳን የመከላከያ ቁሳቁሶች ማምርቻ ድርጅት አከሰሜን ኮሪያ ጋር የተፈራረማቸውን የውል ስምምነቶች ሙሉ በመሉ ማቋረጧን ገልጻለች። ከዚህ በኋላም ሱዳን ከሰሜን ኮሪያ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ግንኙነት እንደማይኖራት የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጿል። ውሳኔው ካርቱም ፒያንግያንግ የኒውክሌር ፕሮግራሟን እንድታቋርጥ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እየተደረገ ያለውን ጫና የሚደግፍ መሆኑም ነው…

ትናንት ከሰዓት በኋላ ጠፍቶ የነበረው የኬኒያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ ተገኘ

ትናንት ከሰዓት በኋላ ጠፍቶ የነበረው የኬኒያ አነስተኛ የግል የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ መገኘቱ ተገልጿል። የኬኒያ መንገደኞች ባለስልጣን የሆኑት ፓውል ማሪንጋ እንደተናገሩት አውሮፕላኑ በኬኒያ ማዕከል አካባቢ በሚገኘው አበርዳረስ ጫካ ውስጥ ተከስክሶ ተገኝቷል። ይሁን እንጂ በውስጡ የነበሩ የሁለት አብራሪዎችና የ8 ተሳፋሪዎች እጣ ፈንታ እስካሁን ምን እንደሆነ ያለመታወቁ ነው የተገለጸው። አደጋው ከመድረሱ በፊት አውሮፕላኑ በ11ሺህ900 ጫማ ከፍታ ላይ ይበር…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጀነራል ሰዓረ መኮንንን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም አድርገው ሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጀነራል ሰዓረ መኮንንን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም አደርገው ሾሙ። ላለፉት ዓመታት በጠቅላይ ኢታማዡር ሹምነት ሲያገለግሉ የነበሩት ጀነራል ሳሞራ የኑስ በክብር ተሸኝተዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ቀደም ሲል ወታደራዊ ማእረጋቸው ተነጥቆባቸው የነበሩት ሜጀር ጀነራል ዓለምእሸት ደግፌ እና ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ማእረጋቸው ተመልሶላቸው…

በኢትዮ- ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የሃገራቱን ግንኙነት የሚያሻሽል ነው – ጠ/ሚ ዶክተር አብይ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የኢትዮ- ኤርትራን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የሚያሻሽል መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በተጀመረው 4ኛው ሃገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጉባኤ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባሳላፈው ውሳኔ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የተላለፈው ውሳኔም ሁለቱ ሃገራት ባለፉት አመታት የነበራቸውን ግንኙነት…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram