በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን የምግብ ዋስና ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ

የሀገሪቱን የእድገት ጎዳና ከግብ ለማድረስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ። የአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛው ዙር የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ ሲጀመር፥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እና ድህነትንም ከስሩ በመናድ ተደማሪ የልማት አቅም መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። መንግስትም የእነዚህን…

የተሽከርካሪ አደጋን ለመቀነስ በ300 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተሰራ ነው

በኢትዮጵያ እየደረሰ የሚገኘውን አስከፊ የትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚያስችል ፕሮጀክት በ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር  ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ። የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሸን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኛው ፥ ፕሮጀክቱ ከተያዘው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን፥ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከዓለም ባንክ በብድር መገኘቱን ተናግረዋል። በዚህ ፕሮጀክትም በተገኘው ብድር በመጠቀም በሀገር አቀፍ ደረጃ የትራፊክ…

አዲሱ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ቃለ መሃላ ፈጸሙ

አዲሱ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ቃለ መሃላ ፈጸሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሳንቼዝ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራሆይ በስፔን ፓርላማ የመተማመኛ ድምጽ ማጣታቸውን ተከትሎ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት። ፔድሮ ሳንቼዝ ዛሬ በስፔን ንጉስ ፊሊፔ 6ኛ አማካኝነት ቃለ መሃላውን ፈጽመዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃገራቸውን በታማኝነት እንደሚያገለግሉ በቃለ መሃላው ወቅት ተናግረዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራሆይ ከፓርቲያቸው የሙስና…

አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አቶ ኢሳያስ ጂራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ባካሄደው ሁለተኛው ዙር ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ምርጫ አቶ ኢሳያስ 87 ድምፅ በማግኘት ነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት። ከአቶ ኢሳያስ ጋር የተወዳደሩት አቶ ተካ አስፋው ሲሆኑ፥ 58 ድምፅ በማግኘት ሁለተኛ ሁነዋል። ከምሳ ሰዓት በፊት በተካሄድው የፕሬዚዳንት ምርጫ አቶ ኢሳያስ ጂራ…

በህክምና ስህተት ያልጋ ቁራኛ የሆነውን መሀመድ አብዲላዚዝ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የህክምና ቡድን ወደ ሳዑዲ ማቅናቱ ተገለፀ

በህክምና ስህተት ያልጋ ቁራኛ የሆነውን መሀመድ አብዲላዚዝ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የሃኪሞች ቡንድን ወደ ሳዑዲ ማቅናቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያቀናው ቡድን ሀኪሞችና ነርሶችን የያዘ ሲሆን፥ ቡድኑ ታዳጊው እንደጎበኘ እና ህፃኑን ለመመለስ የሚያስችል ምርመራም ማድረጉ ተገልጿል፡፡ መሃመድ አብዱላዚዝን ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን ማሳረፊያ የሚቆይ ሲሆን፥ የቤት ውስጥ እንክብካቤ…

ለአቶ መላኩ ፈንታ የሁለት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መኪና ተበረከተላቸው

ዛሬ – አቶ መላኩ ፋንታ ጎንደር ከተማ ገብተዋል፡፡ የጎንደር ከተማ ከንቲባና የመንግሥት ሹማምንት የደመቀ አቀባበል አድረገውላቸዋል፡፡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጎንደር ተወላጆች ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ የሚያወጣ ዘመናዊ የቤት መኪና ለአቶ መላኩ ፈንታ ስጦታ ይሆን ዘንድ አበርክተዋል፡፡ ምንጭ፡- አማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት    

ሰበር ዜና – መቀመጫው በአሜሪካ ያደረገው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ሊከፍት ነው

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የማኔጅመንት አባልና የኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሞሐመድ አብዶሽ በመንገድ ላይ ነን ብለዋል፡፡ ላለፉት አራት አመታት መቀመጫውን አሜሪካ ሴንት ፖል ሚኔሶታ ላርፐንተር ጎዳና ላይ በማድረግ በሳተላይት የቴሌቪዥ ስርጭቱን እያከሄደ የሚገኘውና በጃዋር መሃመድ የሚመራው Oromia Media Network ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ መክፈት በሚቻልበት መንገድ ለመነጋገር ልዑካኑን ወደ አዲስ አበባ ልኳል። የቴሌቪዥን ተቋሙ የማኔጅመንት…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram