በሜክሲኮ በጦር መሳሪያ በተፈፀመ ጥቃት 6 ትራፊክ ፖሊሶች ሞቱ

ታጣቂዎች በሜክሲኮ በፈፀመው ጥቃት የስድሰት ትራፊክ ፖሊሶች ህይወት ማለፉ ተነግሯል። ጥቃቱ ሳላማንካ በተባለች የሜክሲኮ ከተማ የተፈፀመ ሲሆን፥ ከቅርብ ወራት ደዊህ በሜክሲኮ ከተፈፀሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች የሞቱበት መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። ስድስቱ የትራፊክ ፖሊሶች መደበኛ የሆነውን የቁጥጥር ስራ በማከናወን ላይ እያሉ በተከፈተባቸው ጥቃት መሞታቸውን ነው የሳላማንካ ከተማ የመንግስት ባለስልጣን የተናገሩት። ትራፊክ ፖሊሶቹ በምን ምክንያት ተገደሉ የሚለው…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ ነገ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን የፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ ነገ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ይካሄዳል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዩ አራት 4 የሚመሩት ፕሬዚዳንት እና ስራ አፈጻሚ አባላትን ለመምረጥ ከመስከረም 30 ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይደረግ መቆይቱ ይታወሳል። ሆኖም ግን ፊፋ ምርጫው በአስቸኳይ እንዲካሄድ አስገደጅ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ምርጫው ነገ ግንቦት 26 በአፋር ክልል ሰመራ ሊደረግ የመጨረሻ…

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ

ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ። ምክር ቤቱ በስብሰባው የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ገምግሟል። አሁን ላይም በሀገሪቱ ስርዓት ሰፍኖ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር…

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ የ2ኛ ዙር መስክ ምልከታ ግኝት ሪፖርት ይፋ አደረገ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በሁለተኛው ዙር የመስክ ምልከታ ግኝቶችን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል። የመርማሪ ቦርዱ ስብሳቢ አቶ ታደሰ ሆርዶፋ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፥ መርማሪ ቦርዱ በሁለተኛ ዙር በአማራ እና በደቡብ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ ምልከታ አድረጓል። በምልከታው በኮማንድ ፖስት ቀጣና አንድ እና ቀጠና አምስት በሚገኙ 31 የማቆያ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ ተመልክቷል። በእነዚህ ማቆያ…

ለጤና አስፈላጊ ያልሆኑ ልማዶች

የአለም ጤና ድርጅት ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው የሀገሮቹ ነበራዊ ሁኔታ የሚለያይ ቢሆንም በህክምናው ዘርፍ በመጣው ለውጥ የሰው ልጅ ከፍተኛው የመኖሪያ እድሜ 71 ነው ይላል። ውጤታማ ህክምና እና ክትባቶች በሽታዎችን በመከላከል ረጅም እድሜ ለመኖር እድል መፍጠራቸው ይነገራል። ከህክምናው ባለፈ የስራ ቦታን የተሻለ ማድረግ እና የንፅህና አጠባበቅ ላይ ግንዛቤ መፍጠር መቻል የሰው ልጅ የመኖሪያ እድሜ እንዳሳደገው ነው የሚነገረው።…

አሊባባ ኩባንያ ከ100 የተለያዩ ሬስቶራንቶች ውስጥ የሚታዘዙ ምግቦችን ለደንበኞቹ በድሮን ያሉበት ቦታ ድረስ ማቅረብ ጀመረ

በቻይና ሻንግሃይ በበርካታ ዘርፎች በሀገሪቱ ተሰማርቶ ያለው አሊባባ ኩባንያ በድሮን አገልግሎት የታዘዘበት ቦታ ድረስ ምግቦችን ማቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የሀገሪቱ መንግስት ከሻንጋይ ኢንዱስትራይል ፓርክ አቅጣጫ በሚገኙ 17 የተለያዩ መስመሮች ላይ እንዲሰራ ነው ፍቃድ መስጠቱ የታወቀው፡፡ እነዚህ 17 መስመሮች በጥቅሉ ከ 57 ስኬዌር ኬሎሜትር በላይ ይሸፍናሉ ተብሏል፡፡ ከኢንዱስትሪል ፓርኩ በሚገኙ 100 የተለያዩ ሬስቶራንቶች ውስጥ በአንዱ ደንበኞች ትዕዛዛቸውን…

በአፋር ክልል በተከሰተ የአተት በሽታ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአፋር ክልል በተከሰተ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአፋር ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ። ጤና ቢሮው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀ የአተት በሽታው በክልሉ አራት ወረዳዎች ተከስቷል። በክልሉ ጤና ቢሮ የህክምና ጤና ክብካቤ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሁሴን መሐመድ ሟቾቹ ከሚሌ ወረዳ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ በሚገኙ ወረዳዎች የአተት በሽታ መስተዋሉ…

በአሪዞና የሚገኙ ተላላኪ ሮቦቶች ከእግረኞች እኩል መብት ተሰጣቸው

በዩናይትድ ስቴትስ አሪዞና ግዛት ውስጥ የሚገኙ የእግረኛ መንገድ ተጠቃሚ ተላላኪ ሮቦቶች ከተጓዦች እኩል መብት ተሰጣቸው፡፡ ከዚህ ቀደም ሞተር ሳይክልን ጨምሮ ሮቦቶች እንዲሁም ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች እግረኛ መንገድ እንዳይጠቀሙ የሚል ህግ ነበር፡፡ በዚህ ወር መጀመሪያ ታዲያ በአሪዞና ገዢ የጸደቀው አዲስ ህግ የእግረኛ መንገድን እንዲጠቀሙ የሚፈቅድ ነው፡፡ አዲስ የወጣው ህግ በአሪዞና የሚገኘውን የተላላኪ ሮቦቶችን ገበያ የበለጠ ያሻሽለዋል…

የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ ‘‘አይሪስ’’ የተባለው የዓይን ክፍል ይፋ ሆነ

የመጀመሪው ሰው ሰራሽ ‘‘አይሪስ’’ የተባለው የአይን ክፍል ይፋ መሆኑን የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አረጋግጧል። የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ለዚሁ ቴክኖሎጂ እውቀና የሰጠውም በ389 ያህል ሰዎች ላይ ስኬታማ የህክምና ውጤት ከታየ በኋላ ነው ተብሏል። ህክምናው ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 70 በመቶ ያህሉ እይታቸው ላይ ቀደም ሲል ተከስቶ የነበረው ችግር የተቃለለ መሆነኑን ሲያስረዱ 94 በመቶ ያህሉ ደግሞ በአይናቸው…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram