አነስተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገው 5ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጣ

አነስተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገው 5ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በዛሬው እለት ወጥቷል። የእጣ አወጣጡ ስነስርአት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድርባ ኩማ በተገኙበት ነው በዛሬው እለት የተካሄደው። በእጣ ማውጣቱ ላይ የተገኙት ከንቲባ ድሪባ ኩማ፥ ከ176 ሺህ በላይ ቤቶችን እስካሁን ለተጠቃሚ ያስተላለፈው የከተማው አስተዳደር አሁንም ከ132 ሺህ በላይ ቤቶችን በግንባታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።…

Advertisements

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ

ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ። ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሳ ነው የውሳኔ ሀሳቡን ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። የሚኒስትሮች ምክር…

የህዝብ ለውጥ ፍላጎትን ማንም አያቆመውም- መንግስት

የህዝብ ለውጥ ፍላጎትን ማንም አያቆመውም አለ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሳምንታዊ የመንግስት የአቋም መግለጫው። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል። የህዝብን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በኢትዮጵያ የተጀመረው ፈጣን ለውጥ ተጨባጭ ስኬቶችን ማስመዝገብ በመቻሉ አሁን ላይ ለውጡን ማንም ሊያቆመው በማይችለው ደረጃ ላይ ደርሷል። ባለፉት ጥቂት ወራት መንግስት አገራዊና ከባቢያዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ እየወሰዳቸው ባሉ እርምጃዎች ፈጣንና ተጨባጭ…

በግል ጤና ተቋማት ያለውን ከፍተኛ የወሊድ አገልግሎት ክፍያ ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው

በግል ጤና ተቋማት ያለውን ከፍተኛ የወሊድ አገልግሎት ክፍያ ለመቆጣጠር ጤና ጣቢያዎችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ነው። በመዲናዋ የግል የህክምና ተቋማት ለቀዶ ህክምና የወሊድ አገልግሎት ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ ብር ሲያስከፍሉ ይስተዋላል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የፈውስና ተሀድሶ ህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አባስ ሀሰን፥ ችግሩን ለመቆጣጠር ጤና ጣቢያዎችን በሰው ሀይል እና በመሳሪያ የማደራጀት ስራ…

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና የመከላከያ ሚኒስቴር በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ በትብብር በሚሰሩበት ጉዳዮች ዙሪያ በትናንትናው እለት ተወያይተዋል። በውይይታቸው ወቅትም ሁለቱ ተቋማት እንደከዚህ በፊቱ በትብብር የሚሰሩበትን ሁኔታ አጠናክረው ለመቀጠል ከስምምነት መድረሳቸውም ተገልጿል። ተቋማቱ የመረጃ መሰብሰቢያ፣ መተንተኛ እና ማሰራጫ ስርዓቶችን በማዘመን ረገድ በጋራ ለመስራት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል። በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል…

የጅማ፣ ባህርዳር፣ ድሬደዋ፣ ሀዋሳ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራና ሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው

በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው እለት ተማሪዎቻቸውን በማስመረቅ ላይ ይገኛሉ። የጅማ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው። ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 556 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 620 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 4 ተማሪዎችን በሶስተኛ ወይም ዶክትሬት ዲግሪ እያስመረቀ ነው። የባርዳር ዩኒቨርሲቲም በዛሬው እለት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 11 ሺህ…

ደብረ ብርሃንና ወልዲያን ጨምሮ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እያመጧቸው ያሉ ለውጦችን በመደገፍ በአማራ ክልል በሚገኙ በርካታ ከተሞች በዛሬው እለት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ሰልፉ በዛሬው እለትም ደብረ ብርሃን እና ወልዲያ ከተሞችን ጨምሮ በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ነው እየተካሄደ ያለው። የሰልፉ ዓላማም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እያመጧቸው ያሉ ለውጦችን ለመደገፍ ምስጋና ለማቅረብ ነው እየተካሄደ ያለው። በተጨማሪም ሰኔ 16 ቀን…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram