ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሐኪሞች ከታካሚዎች ጋር እንዲግባቡ ለሦስት ወራት የሚቆይ የኦሮምኛ ቋንቋ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሐኪሞች ከታካሚዎች ጋር እንዲግባቡ ለሦስት ወራት የሚቆይ የኦሮምኛ ቋንቋ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ስልጠናው ከታካሚዎች ጋር ተግባብተው እንዲሰሩና ጊዜን ለመቆጠብ እንደሚረዳቸው ሰልጣኞች የገለጹ ሲሆን፥ ታማሚው ሀኪሙ ተረድቶኛል ብሎ እምነት እንዲጥል እንደሚያደርግውም ተገልጿል። በሆስፒታሉ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት 70 በመቶ የሚሆኑት ታካሚዎች ከኦሮሚያ ክልል የሚመጡ መሆኑን ያሳያል ብለዋል የስልጠናው ዋና አስተባባሪ ዶክተር ቶማስ መኩሪያ። ከነዚህም…

የዶ/ር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣት አንደምታዎች

ካለፉት ሦስት ዓመታት አንስቶ፥ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ወደ ስልጣን እስከመጡበት ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያችን ክፉኛ ታማ ከርማለች። ሀገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ህመሟ ሽሮ ከተጣባት ክፉ ደዌ ተፈውሳለች ባይባልም፤ እነሆ የጠ/ሚ አብይ ወደ ስልጣን መምጣት በጎ አጋጣሚ ሆኖላት፣ ቢያንስ ከህመሟ እያገገመች እንደምትገኝ ለማየት በቅተናል። እነኛን የከፉ ሦስት ዓመታት፣ ዛሬ ላይ ቆመን የኋሊት ስናስታውሳቸው፤ ሀገራዊ ስንክሳሮቻችን…

ሳዑዲ አረቢያዊው አልቢትር ከአለም ዋንጫ ውጪ ሆኑ

የፊፋ የዳኞች ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ሳዑዲ አረቢያዊውን አልቢትር ፉዓድ አል ሚርዳሲን ከሩሲያው ዓለም ዋንጫ ዳኝነት መቀነሳቸውን ይፋ አደረገ፡፡ ከዋና አልቢትር በተጨማሪም ሁለት ረዳት አልቢትሮችም መቀነሳቸውን አስታውቋል፡፡ ረዳት ዳኞቹ ከዋና አልቢትር ጋር በመሆን አንድ ላይ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ይመራሉተብሎ ነበር፡፡ ፊፋ ስለጉዳዩ ለሳዑዲ አረቢያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና ለእስያ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን አሳውቋል፡፡ ዋና አልቢትሩን ለመተካት እስከአሁን እንቅስቃሴ ያለማድረጉን ጠቅሶ፥ ውድድሩን እንዲመሩ ሁለት ረዳት አልቢትሮችን መተካቱን ገልጿል፡፡ ፊፋ አልቢትሩን…

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተዋቀረ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች መዋቀሩን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታወቀ፡፡ ይህም ቀደም ሲል በማዕከል ብቻ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች በቅርበት ለህብረተሰቡ መስጠት በማሰብ በክልሎች በአዲስ መልኩ መዋቀሩን ነዉ የሳይንስና ቴክኖሎለጅ ሚኒስተር እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ የገለጹት። በአዲስ መልኩ ለተዋቀሩት አገልግሎቶች ምክትል ስራ አስፈፃሚ የተሾመላቸዉ ሲሆን፥ ተጠሪነታቸዉም ለክልል አስተዳደሮች እና…

በመዲናዋ የሚኒባስና የሀይገር ባስ የትራንስፖርት የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን አዲስ የኪሎ ሜትር ልኬት በማድረግ በሚኒ ባስ እና የሃይገር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ። ማሻሻያው የከተማ ትራንስፖርት በሚሰጡ መደበኛ ታክሲዎች (ሚኒባሶች) እና የሃይገር ባሶች የትራንስፖርት ክፍያ ላይ የተደረገ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል። ባለስልጣኑ ማሻሻያው በአገልግሎት ሰጭ እና ተገልጋዩ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታትና ያለውን የትራንስፖርት ፍላጎትና አቅርቦት ለማጣጣም…

Ethiopia To Adopt Visa-Free Policy For All African Visitors

Ethiopia will soon allow all Africans to visit the country without visas, according to Prime Minister Abiy Ahmed. After Rwanda’s decision to allow African to enter the country without a visa. The issuance of visa-on-arrival for all countries was widely applauded by many across the continent. Speaking during a state banquet for Paul Kagame last…

ተስፋ ሰጪው የአእምሮ ካንሰር ክትባት…

ተመራማሪዎች በአእምሮ ካንሰር የተጠቁ ሰዎችን በህይወት እንዲቆዩ ይረዳል በሚል የሰሩት ክትባት ወደ ሙከራ ደረጃ መግባቱ ተነግሯል። በሙከራውም በአእምሮ ካንሰር የተጠቁ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ተደርጓል የተባለ ሲሆን፥ በዚህም ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ካልወሰዱት ጋር ሲነፃፀሩ በህይወት የመቆየት እድላቸው በሁለት እጥፍ ጨምሮ ተገኝቷል። አዲሱ ክትባት የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ስርአት ኢላማውን የአእምሮ ካንሰር ላይ አድርጎ እንዲያጠቃ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።…

በኤርትራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ33 ሰዎች ህይወት አለፈ

በማዕከላዊ ኤርትራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቷ ሚዲያ አስታወቀ፡፡ እንዲሁም በአደጋው ምክንት 11 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡ አደጋው የደረሰው ከአስመራ ወደ ከረን ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ ምክንያት ሲሆን 80 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል በመግባቱ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የህዝብ ማመላለሻው ለሃይማኖታዊ ጉዞ 45 ሰዎችን ይዞ በመጓዝ ላይ እንደነበረ ተገልጿል፡፡ ፖሊስ…

አሜሪካና ሜክሲኮ ዳግም በድንበር አጥር ምክንያት ተወዛገቡ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሜክሲኮን ህገወጥ ስደተኞችን ባለመከላከሏ ወቅሰው፥ በድጋሚ የድንበር አጥሩን በራሷ ወጪ እንደምትገነባ ገልጸዋል፡፡ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሊያከናውኗቸው ቃል ከገቧቸው ጉዳዮች መካከል በሀገራቸውና በሜክሲኮ ድንበር መካከል አጥር መገንባት አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ታዲያ አጥሩ የሚገነባው በሜክሲኮ መንግስት በጀት እንደሆነ ገልጸው ነበር ሆኖም ከሜክሲኮ በኩል ጠንካራ ተቃውሞ ሲገጥማቸው ከርሟል፡፡ ይህ ተቀዛቅዞ የነበረውን ጉዳይ…

የ10ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው

የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2010 ዓ.ም ሃገር አቀፍ ፈተና መውሰድ ጀመሩ። የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል። ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ የሚሰጥ ይሆናል። ፈተናውን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች እንደሚወስዱ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታውቋል። ፈተናው በመላ ሃገሪቱ በተቋቋሙ 2 ሺህ 709 የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል። የ12ኛ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram