ኬንያ እጃቸውን በሙስና ቅሌት አስገብተዋል ያለቻቸውን ሀላፊዎች በስር ቁጥጥር ማዋል ጀመረች

ኬንያ እጃቸውን በሙስና ቅሌት አስገብተዋል ያለቻቸውን ሀላፊዎች በስር ቁጥጥር ማዋል ጀመረች፡፡ 78 ሚሊዮን ዶላር መዝብረዋል ያለችውን ሀላፊ በቁጥጥር ስር በማዋል ከ40 በላይ ሃላፊዎች ላይ ክስ መስርታች፡፡ የኬንያ ፖሊሶች 8 ቢሊየን ሺሊንግ ወይም 78 ሚሊዮን ዶላር ሙስና ፈፀሙ የተባሉትን የሀገሪቱ ወጣቶች ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩን በቁጥጥር ስር አውሎታል። ብሔራዊ የወጣት አገልግሎት (ኒውስ) ዋና ዳይሬክተር ሪቻርድ ኑዱቤን በቁጥጥር…

የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣን ወደ አሜሪካ ማቅናታቸው ተነገረ

ከሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንዱ የሆኑት ጄነራል ኪም ዮንግ ቾል ወደ አሜሪካ ማቅናታቸው ተነገረ። ባለስልጣኑ ወደ አሜሪካ ያቀኑት በአሜሪካ እና ሰሜን ኮሪያ መሪዎች መካከል ሊካሄድ እቅድ ለተያዘለት ውይይት ዙሪያ ለመምከር መሆኑም ተሰምቷል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጄነራል ኪም ዮንግ ቾል ለውይይት ወደ አሜሪካ እየመጡ መሆኑን በዛሬው እለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አረጋግጠዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም ከጄነራል ኪም…

ሀንጋሪ ለስደተኞች ድጋፍ ማድረግን ወንጀል አድርጋ በህግ ልታፀድቅ ነው

የሀንጋሪ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ለሚሞክሩ ህገ ወጥ ስደተኞች ድጋፍ ማድረግ ወንጀል እንዲሆን የሚያስችል ህግ ሊታፀድቅ ነው። ረቂቁ ህግ ሆኖ የሚፀድቅ ከሆነ የመኖሪያ ፍቃድ ለሚጠይቁ ስደተኞች በበራሪ ወረቀት መረጃ፣ ምግብ እንዲሁም የህግ ምክር አገልግሎት የሚያቀርቡ አካላት በወንጀል ይጠየቃሉ ተብሏል። ከዚህ ባለፈ የአውሮፓ ሀገራት የመኖሪያ ፈቃድ የሚፈልጉ ስደተኞች ወደ ሀንጋሪ እንዳይልኩ ለማድረግ ሀገሪቱ የህገ መንግስት ማሻሻያ…

ናይጄሪያ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መወዳደሪያ እድሜ ገደብን ወደ 35 ዝቅ የሚያደርግ ህግ ልታፀድቅ ነው

የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሀሙድ ቡሃሬ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ የተቀመጠውን የእድሜ ገደብ መቀነስ የሚያስችል አዲስ ህግ እንደሚፀድቅ አስታወቁ። አዲሱ ህግ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ 40 ዓመት የነበረውን የእድሜ ገደብ ወደ 35 እንዲሁም የሴናተር እና የክልሎች አስተዳዳሪ መወዳደሪያ እድሜ ገደብን ከ3o ጀምሮ እንዲሆን ያደርጋል። ይህ ህግ ወጣቶች በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ መሳተፍ እንዲችሉ እድል ይፈጥርላቸዋል ተብሏል። ውሳኔው ወጣቶች ከሀገሪቱ…

የጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃ/ወልድ የመጨረሻ ቀናት በቤተሰቦቻቸው ሲገለጽ

ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰው ሲሆኑ በ ጣልያን ወረራ ጊዜ አምስቱን ዓመት ሙሉ በፓሪስ የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈጻሚ፤ በዠኔቭ በዓለም መንግሥታት ማኅበር የኢትዮጵያ ዋና ጸሐፊ ከድል በኋላም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት እና እስከ አብዮት ፍንዳታ ድረስም በዓፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር ነበሩ። ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ አቃቂ ታስረው ከቆዩ በኋላ ያለፍርድ ኅዳር ፲፬ ቀን…

የፈረንሳይ አጫሾች ቁጥር በ1 ዓመት ውስጥ በ1 ሚሊየን ያህል አሃዝ ቀነሰ- ጥናት

የፈረንሳይ አጫሾች ቁጥር በአንድ አመት ውስጥ በ1 ሚሊየን ያህል አሃዝ እንደቀነሰ አንድ ጥናት አመላክቷል። በፈረንሳይ የጫሾቹ ቁጥር በእየቀኑ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን፥ ከፈረንጆቹ 2016- 2017 ባሉት ጊዚያት መካከል 1 ሚሊየን ያህል ዜጎች ማጨሳቸውን ያቆሙ መሆኑ ነው የተገለጸው። በለፉት 10 አመታት በፈረንሳይ የአጫሾች ቁጥር በዚህ ደረጃ ሲቀንስ ይህ የመጀመሪያው ሲሆን፥ የአጫሾቹን ቁጥር በዚህ ደረጃ ለመቀነስ ያስቻለው ቀደም…

የአምስቱ የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ B-787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች የማኔጅመንቱ ድብቅ ቁማር

ANA (All Nippon Airways) በመባል የሚታወቀው የጃፖኑ አየር መንገድ ከቦይንግ ካዘዛቸው በርካታ ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ውስጥ ቀድመው ተመርተው የነበሩት B787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች በነበራቸው የምርት ጥራት ችግር የዲዛይን ደረጃቸውን ስለማያሞሉ እና በዚሁም ምክንያት አውሮፕላኖቹ ምንም ሳይጭኑ ከባድ በመሆናቸው እና የጭነት መጠናቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ የነዳጅ ፍጆታቸው ከፍተኛ በመሆኑ እና አጭር ርቀት ብቻ መብረር በመቻላቸው በመሳሰሉ ትክክለኛ…

የደቡበ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ነገ ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ። በቆይታቸው ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው በደቡብ ሱዳን ሰላም ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል። የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የሁለተኛውን ዙር የሰላም ሂደት ማሳለጫ ድርድር አዲስ አበባ ውስጥ ማድረጋቸው ይታወሳል። የፖለቲካ ኃይሎቹ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዲያከብሩ ማረጋገጫ ሰጥቷል። የኢጋድ የሚኒስትሮች…

ተቀማጭነታቸው በውጭ ሀገር የሆኑ ሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና ሁለት ግለሰቦች ክስ ተቋረጠ

የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተቀማጭነታቸው በውጭ ሀገር በሆነው ኢሳት እና ኦ ኤም ኤን የተባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲሁም በዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር መሀመድ ላይ የከፈተው ክስ እንዲቋረጥ ጠይቋል። በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ሀገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአዋጅ ቁጥር 943//08 አንቀፅ 6 ንዑስ…

ልጃቸውን በወለዱ 21 ሰዓታት ውስጥ በተማሪዎች የኮሌጅ ምረቃ ፕሮግራም ላይ የተገኙት እናት

በሚኒሶታ ዜናብ የተባሉት እናት 2ኛ ሴት ልጃቸውን በተገላገሉ 21 ሰዓታት ውስጥ የኮሌጅ የተማሪዎች ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ መገኘታቸው ተገልጿል። አሁን ላይ ልጂም ጤና እናትም ደህና መሆናቸውን ያስነበበው ዘገባው የ26 ዓመቷ ዜናብ አብደላ ከተገላገሉ 21 ሰዓት በኋላ የ2ኛ ዲግሪ ዲፕሎማቸውን ለመውሰድ የተማሪዎች የኮሌጅ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል ተብሏል። ዜናብ ከቤተሰቦቻቸው መካከል በትመህርት ከዚህ ደረጃ ለመድረስ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram