ዶክተር አብይ አህመድ 6 ነጥብ ያለው መልእክት አስተላለፉ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው “ከጎረቤቶቻችን እና ከቅርብ ሩቅ ወዳጆቻችን ጋርም ያሉ ክፍተቶችን በእርቅ እና በይቅርታ የማከም የጋራ ባህል እንዲኖረን በጽናት መስጠትን መለማመድ ይገባናል፡፡” ያሉ ሲሆን “ይህች የምንሳሳላት እና የምንወዳት ሀገራችን ሰላም የምትሆነው፣ ጋራ ሸንተረሯ የሞት ሲላ የሚዞረው ሳይሆን የሰላም ምሳሌዎቹ እርግቦች በጣፋጭ ዜማቸው ዙሪያ ገባው የሚደምቀው፣ ከራሳችን ጋር ስንታረቅ፤ ከወዳጅ ዘመድ ጋር ይቅር ስንባባል ብቻ ነው፡፡”…

እውነት ድግምት ይሰራል? በYona Bir

ኃይሌ ገብረስላሴ ስለ ጌጤ ዋሚ ቪዲዮ የሰጠውን አስተያየት አደመጥኩ። እንደተለመደው አስተያየቱ ከብዙ ሰዎች ውግዘትን አስከትሎበታል። ኃይሌ እንደሆነ አይሞቀው አይበርደው። ፈረንጆቹ እንደሚሉት “he speaks his mind”… ይቻመው!!! በፌስቡክ የተለቀቀው ቪድዮ አትሌት ጌጤ ዋሚ በመምህር ግርማ መቁጥሪያ እየተደበደብች ድግምት ተድረገብኝ ብላ ስትለፈልፍ ያሳያል። ቪዲዮው እንደ ብዙዎቹ የሰይጣን ማስወጣት ድራማዎች እጅግ ያሳዝናል። ኃይሌ ግን እንደ ብዙዎቻችን አዝኖ ዝም…

አፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ ራሳቸውን በክብር ያጠፉበት ሽጉጥ በአንድ የፈጠራ ባለቤት ተሰርቶ ሙዝየም ገባ

በ1860 ዓ/ም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ራሳቸውን በክብር ያጠፉበት ሽጉጥ ከታሪክ ሁነቶች ጋር በማገናዘብ ተሰርቶ ትናንትና ወደ ሙዚየም ገብቷል፡፡ የፈጠራው ባለቤት ወጣት ሃይሉ ሽባባው እንደሚለው ሽጉጡ ከዘመን እና ከታሪክ ጋር የተዋኸደ ነው፡፡ ሽጉጡም ከፁሁፍ ሀሳቦች የተቀዳ ሲሆን 20 ሜትር ድረስ መተኮስ ይችላል፡፡ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የባህል እሴቶች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮናስ ይትባረክ ሽጉጡ በታሪክ አጥኝዎች ስምምነት የተሰራ…

የደራው ጨዋታ: ማንም ተናግሮለት የማያውቀው የግንቦት 08,1981 ዓ.ም መፈንቅለ መንግስት ሙከራ

በ1980 ዎቹ የመጀመሪያ ሩብ ዓመታት ውስጥ ደቂቃዎች ይበራሉ። ሰዓታት ቀናትና ወራት ይከንፋሉ። ድርጊቶች ጊዜን ይሻማሉ። ሌትም እንደቀን የእንቅልፍ ወጉን አጥቷል። ክንዋኔዎች እየተቀጣጠሉ እየተሰናሰሉ ወደ ፊት ይገሰግሳሉ። ታሪክ ይሰራል፤ ይገነባል፤ያድጋል። ዓላማ ከሰንደቅ ላይ ከየአቅጣጫው ይውለበለባል። ላንዱ ወገን እንደታቦት ይመለካል። ሌላው እንደ ሰብዓ ሰገል ኮከብ በመሪነት ይታወቃል። መፈክሮች በየከተማው፣ በየጋራው፣ በየሸንተረሩ፣ በየሜዳው፣ በየምሽጉ ያስተጋባሉ። መድፎች ያጓራሉ፤ ሚሳይልና ሮኬት…

20 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ከሄሮይን 50 እጥፍ የሚልቅ አደዛዥ ዕፅ ተያዘ

በዩናትድ ስቴትስ ነብራስካ ግዛት ውስጥ ከሄሮይን 50 እጥፍ የሚልቅ 20 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ አደዛዥ ዕፅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ አደዛዥ ዕፁ ፌንታናይል በመባል የሚታወቅ ሲሆን፥ በ1960ዎቹ ለህክምና አገልግሎት ታስቦ የተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አሁንም ቢሆን በህጋዊ መንገድ በሐኪም ትእዛዝ ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑ ይታወቃል፡፡ የሀገሪቷ መድሐኒት ቁጥጥር ኃላፊ እንዳስታወቀው ከሆነ 26 ሚሊየን ሰዎችን የመግደል አቅም ያለው ነበር…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram