ማየት የተሳናቸውን በምላሳቸው ማየት እንዲችሉ የሚያደርገው ቴክኖሎጂ

በዓለም አቀፍ ደረጃ 258 ሚሊየን ማየተ የተሳናቸው ሰዎች እንዳሉ መረጃዎች የሚያመላከቱ ሲሆን፥ ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና በምላሳቸው ማየት የሚያስችላቸው ፈጠራ ይፋ ሆኗል ተብሏል። በዚህም የሰው ልጂን ስሜት የሚተኩ ሰው ሰራሽ መሳሪዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የሰው ልጆች በተለያዩ አጋጣሚዎች ያጧቸውን ስሜቶች ማጣጣም መቻላቸውም ነው የተገለጸው። የእይታ መረጃዎችን ከአካባቢው በመሰብሰብ ማየት የተሳናቸው ሰዎች ማየት ያልቸሏቸውን ነገሮች በደምጽ ወይንም…

በጋምቤላ ክልል ልማት ይረጋገጥ ዘንድ ወሳኝ የሆነውን ሰላም ለማስፈን የፌደራል መንግስት ከክልሉ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ገለፁ

በጋምቤላ ክልል ልማት እና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ወሳኝ የሆነውን ሰላም ለማስፈን የፌደራል መንግስት ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ እንደሚሰራ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት ጀምሮ በክልሉ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፥ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ውይይት አድርገዋል። ዛሬም በጋምቤላ ስታዲየም ለተሰበሰቡ ለክልሉ ነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመላው የክልሉ ህዝቦች ባስተላለፉት መልዕክት የጋምቤላ ህዝቦች…

ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ምህረት ያደረገላቸው 1 ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። ወደ ሃገር ቤት የተመለሱት ዜጎች የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ለሳዑዲ ዓረቢያ ንጉስ በሃገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞች እንዲፈቱ በጠየቁት መሰረት ምህረት የተደረገላቸው ናቸው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም እና ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር አቀባበል አድርጎላቸዋል። ከዚህ ባለፈም አስፈላጊውን አቅርቦት…

የካርበን ጋዝን ለመሰብሰብ የሚያስችል ቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ ላይ ሊውል ነው

የብሪታኒያው ሊድ ዩንቨርሲቲ ከባዮ ፊውል ሃይል ምንጭ የሚወጣ በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር እንዳይገባ ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ ለማዋል አየሰራ መሆኑ ተገለጸ ። ድራአክስ ሃላፊነቱ የተወሰ ኩባንያ የመጀመሪያውን የአዲሱን ፈጠራ የሙከራ ትግበራ በዚህ ወር በሰሜን ዮርክሺሬ የሃይል ታዳሽ የኤሌክትሪክ ሃይል ፕሮጀከት ጣቢያ አገልግሎት ላይ እንደሚያልም ታውቋል። ቴክኖሎጂው በፈረንጆቹ 2009 የተገኘ የብሪታኒያው ሊድ ዩንቨርሲቲ ፈጠራ…

የደቡብ ኮሪያ መሪ ሙን ጃ ኢን ዛሬ ወደ አሜሪካ ያቀናሉ

የደቡብ ኮሪው መሪ ሙን ጃ ኢን ወደ ዩናትድ ስቴትስ ዛሬ ሊያቀኑ መሆኑ ተነገረ፡፡ የሙን ጉብኝት በዩናትድ ስቴትስና በሰሜን ኮሪያ መካከል ሰሞኑን በተከሰተው አለመግባባት ላይ ለመወያየት ነው ተብሏል፡፡ ሙን በነገው ዕለት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በዋሽንግተን ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን ከሙን ጋር የነበራቸውን ውይይት መሰረዛቸው ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም የአሜሪካ…

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የግሬት ማንቸስተር 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን አሸነፈች

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በዛሬው እለት በእንግሊዟ ማንችስተር የተካሄደውን የግሬት ማንቸስተር 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን አሸነፈች። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩን በ31 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመግባት ነው በአንደኝነት ያጠናቀቀችው። ጥሩነሽን በመከተልም ኬንያዊቷ ጆይስሊን ጆፕጎስኪ በ31 ደቂቃ ከ57 ሰከን ሁለተኛ ስትወጣ፤ ቤትሲይ ሲያና ደግሞ በ32 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ሶስተኛ ወጥታለች።…

የአዕምሮ በሽታን መከላከል የሚያስችል ዘረ መል /በራሂ/ ይፋ ሆነ – ጥናት

ጭንቅላት ውስጥ ያልተፈለገ የፕሮቲን ክምችት መፈጠር ለመርሳት በሽታ እና ሌሎች ተያያዥ የአዕምሮ በሽታዎች የሚያጋልጥ ሲሆን፥ ይህን ችገር ለመከላከል የሚያስችል ‘‘አንክርድ 16’’ የተባለ ዘረ መል/በራሂ/ መግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ። በጥናቱ እንደተገለጸው ‘‘አንክርድ 16’’ የተባለው ዘረ መል /በራሂ/ ያልተፈለጉ የፕሮቲን ውጤቶች ጭንቅላት ውስጥ ከሚፈለገው በላይ እንዳይመረቱና እንዳይከማቹ ያደርጋል ተብሏል። በአዕምሮ ውስጥ የሚከማቹ ያልተፈለጉ የፕሮቲን ውጤቶች የአዕምሮ ነርቭ ሴሎች…

በኦሮሚያ ክልል ከሀሰተኛ የትምህርት ሰነድ ጋር በተያያዘ ከ15 ሺህ ሰራተኞች በላይ ጥቆማ ቀረበባቸው

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በተካሄደ የትምህርት ማስረጃ ሰነድ የማጣራት ስራ ከ15 ሺህ በላይ በክልሉ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ጥቆማ መቅረቡን የኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮ ጥቆማውን በተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም ያሰባሰበ ሲሆን፥ እስከ መጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ጥቆማውን በማጣራት ወንጀሉ የተገኘባቸው ግለሰቦች ከስራ ከማሰናበት ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram