መቐለ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐሌ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ተስታካካይ ጨዋታ  1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት   ተጠናቀቀ። በጨዋታው ባለሜዳዎቹ መቐሌ ከተማዎች በ74ኛው ደቂቃ አማኑኤል ገ/ሜካኤል ባስቆጠራት ግብ መሪ ቢሆኑም አብዱልከሪም ሙሀመድ በ83ኛው ደቂቃ ፈረሰኞችን አቻ ማድረግ ችሏል። ድሬደዋ ከተማ ወላይታ ድቻን ባስተናገደበት ሌላኛው ተስተካካይ ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ። ድሬደዋ ከተማ በረከት ሳምኤል በ41ኛው…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከጋምቤላና ደምቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሳምንቱ መጨረሻ ከጋምቤላና ደምቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ሲያቀኑ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናትም አብረው እንደሚጓዙ ተነግሯል። በደምቢ ዶሎ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም ግንባታቸው የተጠናቀቁትን የደምቢ ዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ…

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን ውስጥ 1 ሺህ ያህሉ ከነገ ጀምሮ ይለቀቃሉ

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን ውስጥ 1 ሺህ ያህሉ ከነገ ጀምሮ እንደሚለቀቁ ተገለፀ። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከሳዑዲ አረቢያ በስልክ እንደተናገሩት፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት በአጠቃላይ ስኬታማ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጉብኝት አንዱ እና ዋነኛ አላማው አድርጎ የነበረው የዜጎች መብት…

ጊና ሀስፔል የመጀመሪያዋ ሴት የሲአይኤ ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

በሲአይኤ የ70 አመታት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጊና ሃስፔል የመጀመሪያዋ ሴት ዳይሬክተር ሆና በአሜሪካ ሴኔት ተሾሙ። ጊና ሃስፔል 100 መቀመጫዎች ባሉት ሴኔት 54 ለ45 በመሆነ ድምፅ ማሸነፍ ብትችልም ከመስከረም 11 የሽብር ጥቃት ጋር ተያይዞ በሽብር በተከሰሱት ላይ የስቃይ ምርምራ እንዲከናወን አድርገዋል የሚል ወቀሳ ይቀርብባቸዋል። ሃስፔል በፈረንጆቹ 2002 የሲአይኤ የታይላንድ ቅርንጫፍ አለቃ በነበረችበት ወቅት የአልቃይዳ የሽብር አባሎች…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በሳዑዲ በህክምና ስህተት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ኢትዮጵያ ታዳጊ ጎበኙ

በሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሀገሪቱ በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና ስህተት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ታዳጊ መሀመድ አብዱልአዚዝን ሆስፒታል በመገኘት ጎብኙ። በዚሁ ጊዜም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለዓመታት ታዳጊውን እያስታመሙ ያሉትን እናት አፅናንተው፤ መንግስት ዜጋውን ለመደገፍ ሁሉንም ጥረት ያደርጋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሳዑዲ አረቢያ ልኡል አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን…

በውጭ አገራት ባንኮች አካውንት ያላቸው ባለስልጣናት በአካውንቶቻቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው – ጠ/ ሚ ዶክተር አብይ

ከባለስልጣናት ጉዞ ጋር በተያያዘም ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተለይም በውጭ አገራት ባንኮች አካውንት ያላቸው ባለስልጣናት በአካውንቶቻቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከትላንት በስቲያ ረፋዱን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለተሰበሰቡ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በስራዎቻቸውና አሰራር ዙሪያ ገለጻና ማሳሰቢያ ሰጡ ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ መድረክ ላይ የራሳቸውን…

ቱርክ ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ 101 ወታደሮች ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ እንደ በአውሮፓውያኑ 2016 ከተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ በርከት ያሉ ወታደሮቿን በቁጥጥር ስር ልታውል መሆኑ ተሰምቷል። በዚህም መሰረት የቱርክ አቃቤ ህጎች በ101 የቱርክ አየር ሀይል አባላት ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣታቸው ነው የተነገረው። የእርስ ማዘዣ የወጣባቸው 101 ተጠርጣሪዎቹ መቀመጫቸውን አሜሪካ ካደረጉት እና በቱርክ መንግስት ከሚፈለጉት የሀይማኖት መሪ ፌቱላህ ጉለን ጋር ግንኙነት አላቸውም ተብሏል። በትናንትናው…

በበራሪ ነፍሳት አምሳል የተሰራችው ገመድ አልባ ሮቦት የመጀመሪያ በረራዋን አደረገች

በራሪ ሮቦቷ እንደ ሌሎች ሰው አልባ ‘‘ድሮኖች’’ ሞተር የተገጠመላት ሳትሆን የንብና መሰል በራሪ ነፍሳቶ ክንፎችን ተመሳስለው በተሰሩ ክንፎች የመጀመሪያ በረራዋን እንዳደረገች ተግልጿል። የዋሽምግተን ዩንቨርሲቲ ስሪት የሆነችው ይህችው ቴክኖሎጂ ከሞተር አገልግሎት ውጭ ‘‘በሴንሰር’’ ለመጀመሪያ ጊዜ መብረር የቻለችው ቴክኖሎጂ አንደሆነችም ነው የተገለጸው። ሮቦቷ በአውስትራሊያ ዓለም አቀፍ ሮቦትና ‘‘አውቶሜሽን’’ ስብሰባ ላይ በሙከራ ደረጃ ለእይታ መቅረቧም ታውቋል። ክንፎቿን ለማንቀሳቀስ…

በሳምንት 2 ጊዜ ዓሳን መመገብ ለልብ ጤና አስፈላጊ እንደሆነ የአሜሪካ የልብ ማህበር ገለጸ

በሳምንት 2 ጊዜ ዓሳን መመገብ ከልብና ከልብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጤና ችግሮችን አንደሚቀንስ የአሜሪካ የልብ ማህበር ገልጿል። ዓሳ ‘‘ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ’’ በተባለው ንጥረ ነገር የበለጸገ በመሆኑ ልብና ከልብ ጋር ተያያዥነተ ያላቸው የጤና ችግሮችን እንደሚቀንስ ነው የተገለጸው። ዓሳን መመገብ ለጤና ያለው ጠቀሜታ ቀደም ሲል የሚታወቅ ቢሆንም የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ቀድሞ ከተደረሰበት ግኝት በላይ ጠቀሜታ ያለው…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram