ጨዋታ ከቴዲ ጋር የመዝናኛ ፕሮግራም ከአርቲስት እና ደራሲ ብርሃኔ ንጉሴ ጋር ያደረገው ቆይታ

Advertisements

Advertisements

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በናይሮቢ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በኬንያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በናይሮቢ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ የኬንያዋ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሞኒካ ጁማ እና በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው፡፡ በነገው ዕለት ይፋዊ ጉብኝታቸውን እንደሚያደርጉ ከጠቅላይ ሚንስትሩ የፌስ ቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ኔቶ የሩሲያን ቆስቋሽነት ለመግታት የአትላንቲክ እዝ አቋቋመ

ሩሲያ ከጊዜ ወደጊዜ የምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ገደቡን አልፎ በአካባቢው ውጥረት እየፈጠረ በመምጣቱ የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ ከአሜሪካ ጋር በመሆን በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የባህር ሃይል ማዘዣ ማቋቋሙን አስታወቀ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ ቀደም ብላ በአካባቢው አሰማርታቸው ከነበሩት የጦር መርከቦች በተጨማሪ ሌሎች የባህር ሃይል መርከቦች ወደስፍራው መላኳን የሀገሪቱ መከላከያ ተቋም ፔንታገን ይፋ አድርጓል ፡፡ የፔንታገን ቃል አቀባይ…

የኬኒያው ምክትል ፕሬዝዳንት በአፍሪካ የመጀመሪያውን የማይክሮሶፍት ማዕከል አስጀመሩ

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ተቋም ማይክሮሶፍት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በመረጃ መረብ ለማገናኘት እንዲረዳ ያቋቋመው የሶፍትዌር ሙከራ ማዕከል በኬኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡ በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የሶፍትዌር ሙከራ ማዕከል ከቴክኖ ብሬይን ሊሚትድ ጋር በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የተከፈተ ሲሆን ለበርካታ ኬኒያውያን የስራ ዕድል ከማስገኘቱ በተጨማሪ ለወጣት መሃንዲሶች የዕውቀት ሽግግር እንደሚያደርግ ይታመናል ፡፡ ማይክሮሶፍት ከህንድ፣ ቻይና እና…

3ሺህ 591 ሰዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወሰነ

ጉዳያቸው በመደበኛው ፍርድ ቤት ይታይ የነበሩ 3591 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲወጡ የአማራ ክልል ካቢኔ ወስኗል፡፡ የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍርዴ ቸሩ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ካቢኔው ይቅርታ እንዲደረግላቸው መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙ፣ሰውን አስገድዶ የሰወረ፣በሙስና ወንጀል የተጠረጠረ፣ሀሰተኛ ገንዝብ ዝውውር ላይ የተሳተፈ፣ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና አስገድዶ መድፈር በመሳሰሉ ወንጀሎች የፈጸመ ታራሚን ይቅርታው አይመለከትም ብለዋል፡፡…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram