ሳዑዲ አረቢያ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል 13 ነጥብ 33 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ይፋ አደረገች

ሳዑዲ በጤና፣ ትምህርት፣ ስፖርት እና በመዝናኛው ዘርፍ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል የ13 ነጥብ 33 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ይፋ አደረገች። በፈረንጆቹ 2020 ተግባራዊ በማድረግ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል የሚያስችላት ሲሆን፥ ለ300 ሺህ ዜጎችም የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል። ለዚህ ፕሮግራም 13 ነጥብ 33 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ 60 በመቶውን መንግስት እና 40 በመቶው የግሉ ዘርፍ እንደሚሸፍን ተነግሯል።…

አትሌት አሊ አብዶሽ መሀመድ ለ4 ዓመታት ከሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ታገደ

አትሌት አሊ አብዶሽ መሀመድ ለ 4 ተከታታይ ዓመታት በማነኛውም ሀገራዊም ይሁን ዓለማቀፋዊ ውድድሮ እንዳይሳተፍ ቅጣት እንተላለፈበት የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። አትሌት አሊ አብዶሽ መሐመድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በታህሳስ ወር 2017 ቻይና ጉዋንዡ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በተደረገው የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ምርመራ የተከለከለ መድኃኒት በመጠቀም የህግ ጥሰት ፈፅሟል። ከዚም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት…

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሀገራት ቡድን ሊቀ-መንበርነትን ተረከበች

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሀገራት ቡድን ሊቀ-መንበርነትን በዚህ ወር በኒውዮርክ ተረከበች። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ የኢትዮጵያ ተጠሪ የሆኑት አምባሳደር ተቀዳ አለሙ ከማሊ አቻቸው ኢሳ ኮንፎሮ ሊቀመንበርነቱን ተረክበዋል። የአፍሪካ ቡድኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ከሚገኙት አምስት ቡድኖች አንዱ ሲሆን፥ እነዚህ ቡድኖች በድርጅቱ ይፋዊ ባልሆነ ሁኔታ ድምፅ ሰጪ እና ተደራዳሪ እንደሆኑ ይነገራል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ…

በአጋርፋ በመንግስት ስር ያለ ስራ የተያዘ 571 ሄክታር መሬት ለ1 ሺህ 252 ወጣቶች ተላለፈ

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በመንግስት ተቋም እጅ ያለ ስራ ከ20 ዓመታት በላይ የቆየ 571 ሄክታር መሬት በዛሬው እለት ለ1 ሺህ 252 ወጣቶች ተከፋፍሏል። መሬቱ በአጋርፋ ወረዳ የሚገኘው የአጋርፋ ግብርና ኮሌጅ ይዞታ የነበረ ሲሆን፥ ከ20 ዓመታት በላይ ምንም ስራ ሳይሰራበት የተቀመጠ ነበር። መሬቱም በዛሬው እለት በ149 ማህበራት ለተደራጁ 1 ሺህ 252 ወጣቶች ተላልፎ የተሰጠ…

አርሰናል በዩሮፓ ሊግ የዋንጫ ህልሙ በአትሌቲኮ ማድሪድ ተጨናገፈ

ትላንት ምሽት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ጨዋታውን ያደረገው አርሰናል 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል፡፡ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገርም በሚቀጥለው የውድድር አመት አርሰናልን ለቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ማድረግ ሳይችሉ ከ22 አመት ቆይታ በኃላ ከክለቡ ጋር ይለያያሉ፡፡ቬንገር በዚህ አመት ያለምንም ዋንጫ ነው ክለባቸውን የሚሰናበቱት፡፡ በጨዋታው ዲያጎ ኮስታ የመጀመሪያ አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሲል ባስቆጠራት ግብ አትሊቲኮ ማድሪድ ለፍጻሜ…

አዲስ አበባና ካርቱምን በባቡር መስመር ለማስተሳሰር የኢትዮጵያና የሱዳን መሪዎች መግባባት ላይ ደረሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለሁለት ቀናት በሱዳን ካርቱም ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናናከር የሚያስችሉ ውይይቶችን ያደረጉት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር ጋር በሱዳን ብሄራዊ ቤተመንግስት በጋራ በሰጡት መግለጫ ፍሬያማ ውይይቶችን ማድጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታከናውናቸው የልማት ተግባራት የታችኛው…

የስዊድን አካዳሚ በ2018 የስነፅሁፍ የኖቤል ሽልማት እንደማይኖር አስታወቀ

አካዳሚው የ2018 የስነፅሁፍ ሎሬትነት የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎችን ከ2019 ጋር ይፋ እንደሚያደርግ ነው የጠቀሰው። አካዳሚው የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት ለማስቀረት የወሰነው በአወዛጋቢ የወሲብ ቅሌቶች ስሙ በመጥፋቱ ነው። በዚህ የወሲብ ቅሌት ውንጀላ ምክንያት የዘንድሮው የስነፅሁፍ ኖቤል ሸላሚ ቦርድ አባላት ከስራ ሃላፊነታቸው መልቀቃቸው ተገልጿል። አወዛጋቢው ክስተት የተቋሙ ዝና እንዲቀንስ ማድረጉንና ህዝቡ በኖቤል ሽልማት ሰጪ ድርጅቱ ያለውን እምነት በመሸርሸሩ የዘንድሮ…

የፊልስጤሙ መሪ መሀሙድ አባስ የፒ.ኤል.ኦ ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

የፊልስጤሙ መሪ መሀሙድ አባስ የፊልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት (ፒ.ኤል.ኦ) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ መመረጣቸው ተነገረ። የፊልስጤም ብሄራዊ ምክር ቤት ለአራት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ ነው መሀሙድ አባስን የፒ.ኤል.ኦ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠው። ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የድርጅቱን የስራ አስፈፃሚ አካላት ምርጫ ያካሄደ ሲሆን፥ በምክር ቤቱ የተመረጦትም በፒ.ኤል.ኦ ከፍተኛ ባለስልጣናት ይሆናሉ ተብሏል።…

የሚያዚያ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ብሏል

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ባለፊው መጋቢት ወር ከነበረበት 15 ነጥብ 2 በመቶ በሚያዚያ ወር ወደ 13 ነጥብ 7 ዝቅ ማለቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በሚያዚያ ወር በምግብ ዋጋ ላይ ቅናሽ የታየ ሲሆን፥ ምግብ ነክ ባልሆኑ ላይ የተወሰነ የዋጋ ጭማሪ መመዝገቡን አመልክቷል። በዚህም በሚያዚያ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት 16 ነጥብ 1…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram