አርባ ምንጭ ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 0 አሸነፈ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታ በአርባ ምንጭ ተካሂደዋል፡፡ አርባ ምንጭ ላይ 9 ሰዓት ላይ የተጫወቱት አርባ ምንጭ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ የመጀመሪያውን የአርባ ምንጭ ግብ አማኑዔል ጎበና ጨዋታው በተጀመረ በአንደኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ ጸጋዬ አበራ በ38ኛው ደቂቃ እንዲሁም እንዳለ ከበደ በ44ተኛው ደቂቃ ላይ ሦስተኛውን ጎል ለአርባ ምንጭ አስቆጥሯል፡፡ ፕሪሚየር ሊጉን ከተከታዮቹ…

‘ኢትዮ-ስፔስ’ የተባለ አዲስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ ተሰራ

ኢትዮ-ስፔስ የተባለ አዲስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ መሰራቱ ተገለፀ። በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተሰራው መተግበሪያው በዚህ ወር ይፋ እንደሚደረግም ታውቋል። አዲሱ መተግበሪያ ተቋሙን ለኀብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ኀብረተሰቡ ስለ ስፔስ ሳይንሱ ያለው ግንዛቤ እንዲያድግ ያግዛል ተብሏል። መተግበሪያው በኢኒስቲቲዩቱ የስፔስ ሳይንስና አፕልኬሽን የስራ ክፍል ረዳት ተመራማሪ በአቶ ዳዊት ካሱ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል። ኢትዮ-ስፔስመተግበሪያ ስለ ኢንስቲትዩቱ መረጃ የሚሰጥ፣ ስፔስን…

የመረጃ መረብ ጠላፊዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ የሆቴል ክፍሎችን የሚከፍት ቁልፍ መስራታቸው ተነገረ

የመረጃ መረብ ጠላፊዎች ያለ አንዳች አሻራ በደቂቃዎች የዓለም ዓቀፍ ሆቴሎች ክፍሎችን በር ለመክፈት የሚያስችል ቁልፍ (ማስተር ኪ) መስራታቸውን የሳይበር ጥቃት ደህንነት ተመራማሪዎች ገለፁ። በፊንላንድ የመረጃ መረብ ደህንነት ኩባንያ የዘረፉ አማካሪ የሆኑት ቶሚ ቱሚኔንና ቲሞ ሂርቮኔን እንደገለፁት “ቪንግ ካርድ ኤልሴፍ” የተባለ ዘመናዊ የሆቴሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁልፎች ላይ ሶፍትዌር ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተረጋግጧል። ኣሳ አብሎይ የተባለው ኩባንያ ምርት…

ተመራማሪዎች ያለገደብ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል አዲስ ፕላስቲክ ሰሩ

የተመራማሪዎች ቡድን በአይነቱ አዲስ የሆነ ፕላስቲክ መስራታቸው ተነግሯል። የኮለራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሰሩት አዲሱ ፕላስቲክ በመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ዘዴ ያለ ገደብ በድግግሞሽ በማምረት ለመጠቀም የሚያስችል ነው። በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር ኢዩጂን ቼን እንደሚናገሩት፥ አዲሱ ግኝት በየዓመቱ የምንጥለውን የፕላስቲክ ቆሻሻ መጠን ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል። በየዓመቱ 12 ሚሊየን ቶን የፕላስቲክ ቆሻሻዎች በውቂያኖሶች ላይ…

በሶሪያ ማንነቱ ባልታወቀ ኃይል የሚሳዔል ጥቃት ደረሰ

በሰሜናዊ ሶሪያ በጦር ሰፈሮች ላይ በደረሰ የሚሳዔል ጥቃት ብዙዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን አስታወቁ፡፡ በጥቃቱም 26 የሚደርሱ የመንግስት ወታደሮች መሞታቸውንና ከ60 በላይ መቁሰላቸውን ተቀማጭነቱ በብሪታንያ የሆነ አንድ ተቆጣጣሪ ድርጅት ገልጿል፡፡ ከሟቾቹ መካካል አራቱ ሶሪያውያን ሲሆን አብዛኞች ደግሞ ኢራናውያን ወታደሮች ናቸው ተብሏል፡፡ እስከአሁን የሚሳዔል ጥቃቱ ከየት እንደተሰነዘረ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ከዚህ ቀደም እስራዔል በተናጠል እንዲሁም አሜሪካና…

በሀገራዊ ምርጫ የፌደራልና የክልል መንግስታት በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢያዙ ግንኙነታቸውን የሚደነግግ የፖሊሲ ማዕቀፍ ፀደቀ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት የተመለከተውን “የመንግስታት ግንኙነት ፖሊሲ ማዕቀፍ”ን አፀደቀ። ዛሬ ለምክር ቤቱ ቀርቦ የፀደቀው በኢፌዴሪ የመንግስታት ግንኙነት የፖሊሲ ማእቀፍን የተመለከተው ሰነድ የሀገሪቱ ህገመንግስት የፌደራል-ክልል እንዲሁም የክልል-ክልል መንግስታት ፖሊሲዎች እና አፈፃፀሞች እንዴት እንደሚሳለጡና እንደሚቀናጁ በዝርዝር እና በግልፅ ሁኔታ እንዳላስቀመጠ አንስቷል። ይህም ሁኔታ የመንግስታት ግንኙነቶች ኢ-መደበኛ፣ ያልተደራጁና ጊዜያዊ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ነው የተመለከተው። በመሆኑም…

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾመ። ወይዘሮ ኬሪያ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ ለምክር ቤቱ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተከትሎ ነው። ምክር ቤቱም ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የቀድሞውን አፈ ጉባኤ የስራ መልቀቂያ ተቀብሎታል። ሹመቱም በሙሉ ድምጽ ፀድቋል። ወይዘሮ ኬሪያ የትግራይ ክልል የሲቪል ሰርቪስ…

Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram