20 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ከሄሮይን 50 እጥፍ የሚልቅ አደዛዥ ዕፅ ተያዘ

በዩናትድ ስቴትስ ነብራስካ ግዛት ውስጥ ከሄሮይን 50 እጥፍ የሚልቅ 20 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ አደዛዥ ዕፅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አደዛዥ ዕፁ ፌንታናይል በመባል የሚታወቅ ሲሆን፥ በ1960ዎቹ ለህክምና አገልግሎት ታስቦ የተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አሁንም ቢሆን በህጋዊ መንገድ በሐኪም ትእዛዝ ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑ ይታወቃል፡፡

የሀገሪቷ መድሐኒት ቁጥጥር ኃላፊ እንዳስታወቀው ከሆነ 26 ሚሊየን ሰዎችን የመግደል አቅም ያለው ነበር ብሏል፡፡

የሀገሪቷ ፖሊስ ብዙ ሰዎችን የመግደል አቅም ያለው ፌንታናይል በዚህ መጠን ሲያዝ በታሪክ መጀመሪያው ነው ብሏል፡፡

ፌንታናይሉ የተያዘው በጭነት መኪና ውስጥ ተሸሽጎ ሲሆን፥ የትራፊክ መብራት ባስቆመው ወቅት መያዙን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

53 ኪሎ ግራሙን ፌንታናይል በማዟዟር የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ በዚህ ዕፅ ምክንያት በየዕለቱ 115 ሰዎች እንደሚሞቱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

 

 

ምንጭ፦አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram