19 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያለው የህንድ ሩጲ በኤቲኤም ውስጥ በመብላት የተጠረጠረችው አይጥ ሙታ እንደተገኘች ተገልጿል።
ህንድ ቲንሱኪያ የተባለ ባንክ ሰራተኞች አንድ አይጥ ኤቲኤም ማሽን ውስጥ ሙታ መገኘቷ ከተገለጸ በኋላ 19 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያለው የህንድ ሩጲ በአይጦች ሊበላ እንደሚችል ገልጸዋል።
ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ሰኔ 11 በአካባቢው የኤቴኤም ማሽን ባለሙያ የህንድ ባንክ ማሽን በሚያስተካክልበት ወቅት አይጧ ሙታ የተገኘች ሲሆን፥ በሞተችው አይጥ ዙሪያም የተበሉ የ500እና 2000 ሩጲ ኖቶች ተገኝተዋል ተብሏል።
ለዚህ ጥፋት በእርግጠኝነት አይጦች ለመሆናቸው ምርመራ እየተደረገ ሲሆን፥ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጉዳዩ ሆን ተብሎ የተፈጸመና ከተጠያቂነት ለማምለጥ የተደረገ መሆኑን እያመላከቱ ነው ተብሏል።
አይጧ በኤሌክተሪክ ገመድ ክፍተት ልትገባ እንደምትችልም ተጠቁሟል።
ምንጭ፦ huffingtonpost.com
የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ
Share your thoughts on this post