በደቡባዊ ጣሊያን ጥናት በማድረግ ላይ የነበሩ የተመራማሪዎች ቡድን የአውሮፓ እድሜ ጠገብ ዛፍ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
ተመራማሪዎች አገኘን ያሉት ዛፍም ቢያንስ 1 ሺህ 230 እድሜ ያለው መሆኑን እና እስካሁንም አድገቱን እንዳላቆመ ነው ይናገራሉ።
“ኢታሉስ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ዛፉ በጣሊያን ፖሊያኖ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፥ ዛፉንም የቱስኪያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ናቸው ያገኙት።
1 ሺህ 230 እድሜ ያለው ያዙ አድሜው በተጨማሪ እስካሁን እድገቱን አለማቆሙ ደግሞ አስገራሚ እንዳደረገው ነው የተነገረው።
“ኢታሉስ” የሚል መጠሪያ ያለው ዛፉ ከዚህ ቀደም በአውሮፓ ውስጥ እድሜ ጠገቡ የተባለው እና በግሪክ የተገኘው ባለ 1 ሺህ 75 ዓመት የደሜ ባለፀጋ ዛፍን በልጦ ነው ባለ ረጅም እድሜ የአውሮፓ ዛፍ የተባለው።
Share your thoughts on this post
Advertisements