fbpx
AMHARIC

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካናዳ፤ አውሮፓ ህብረትና ሜክሲኮ ላይ ሊጥሉ የነበረውን ተጨማሪ ቀረጥ ለጊዜው አራዝመዋል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከካናዳ፤ አውሮፓ ህብረትና ሜክሲኮ ወደ ሃገራቸው በሚገቡ የአልሚኒየምና የብረታ ብረት ምርቶች ላይ ሊጥሉት የነበረውን የታክስ ጭማሪ በመተው ለአንድ ወር ማራዘማቸውን አስታውቀዋል፡፡

እስካሁን የተደረጉት ሁሉም ውይይቶችና ድርድሮች ወደ አሜሪካ የሚገቡ ምርቶችን መጠን መቀነስ፤ ብሄራዊ ደህንነትን መጠበቅ ላይ ያተኮሩ ስለመሆናቸው ከዋይት ሃውስ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በዚህ የአልሙኒየምና የብረታ ብረት ምርቶች ተጨማሪ ቀረጥ ጉዳይ ላይ ከአርጀንቲና፤ ብራዚልና አውስትራሊያ ጋር በመርህ ደረጃ ስምምነት መደረሱም ተገልጿል፡፡

ከደቡብ ኮሪያ ደግሞ ወደ አሜሪካ የምትልከውን የአልሙኒየምና የብረታ ብረት ምርቶችን በ30% የምትቀንስ መጠኑ ያልታወቀ የቀረጥ ቅነሳ እንደሚደረግላት ነው የተነገረው፡፡

አሜሪካ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአለም ዙሪያ ወደ ሃገሯ በሚገቡ የአልሙኒየም ምርቶች ላይ 10% šና የብረታ ብረት ምርቶች ላይ ደግሞ 25% የቀረጥ ጭማሪ መጣሏ የሚታወስ ነው፡፡

ይሁንና ካናዳ፤ የአውሮፓ ህብረትና ሜክሲኮን የመሳሰሉ ሃገራትን ጨምሮ ለጊዜውም ቢሆን ከዚህ ጭማሪ ነጻ እንዲሆኑ ተደርገው ነበር፡፡

በዚህ ጉዳይም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቻይና ጋር በገጠሙት ሙግት በሁለቱ ሃገራት መካከል የንግድ ጦርነት መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በዓለም አቀፍ የንግድ ሂደት ላይም የራሱን ተጽዕኖ እያደረሰ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram