fbpx
AMHARIC

ፕሬዚዳንት ቡሃሪ በቀጣዩ አመት ምርጫ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ

የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ ሃገራቸውን ለሁለተኛ ጊዜ ለመምራት በቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ በብሪታንያ ሊያደርጉ ካሰቡት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ቀደም ብሎ የዛሬ አመት በሚደረገው ምርጫ እንደሚወዳደሩ ተናግረዋል።

የ74 አመቱ ቡሃሪ በፈረንጆቹ 2105 ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታንን በማሸነፍ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ባጋጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ በቀጣይ ጊዜያት በፖለቲካው መስክ ያላቸው ጉዞ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል።

በዛሬው እለት ከፓርቲያቸው አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ግን በቀጣዩ አመት ምርጫ እወዳደራለሁ ብለዋል።

ይህ እቅዳቸው ግን በቀድሞው የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ የተወደደ አይመስልም።

ቀደም ባሉት አመታት ሃገሪቱን የመሩት ኦባሳንጆ፥ ቡሃሪ ከእድሜያቸውና ካላቸው የጤንነት ሁኔታ አንጻር በድጋሚ የመወዳደር እቅዱን ቢሰርዙት መልካም ነው በሚል ግልጽ ደብዳቤ ጽፈውላቸዋል።

ቡሃሪ በቀጣይ ቀናት በብሪታንያ በሚያደርጉት ጉብኝት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይንና የኮመን ዌልዝ አባል ሃገራት ፕሬዚዳንቶችን ያገኛሉ ተብሏል።

ቡሃሪ ከጤንነታቸው ባሻገር የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ማነቃቃትና ጽንፈኛውን ታጣቂ ቡድን ቦኮ ሃራም ቃል በገቡት ልክ መከላከል አልቻሉም በሚል ወቀሳ ይቀርብባቸዋል።

በቀጣዩ አመት በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቡሃሪ ፓርቲያቸው የሆነውን ኦል ፕሮግረሲቭ ኮንግረስን ወክለው ይቀርባሉ።

የእርሳቸው ፓርቲ ዋነኛ ተቃዋሚ የሆነው ፒፕልስ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እስካሁን እጩ አለማቅረቡ ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram