fbpx
AMHARIC

ፍልስጤም ከትራምፕ የቀረበላትን ዕቅድ መቀበል አለባት – የሳዑዲው ልዑል

የሳዑዲ አረቢያው ልዑል መሃመድ ቢን ሰልማን ፍልስጤም ከትራምፕ የቀረበላትን የሰላም ዕቅድ መቀበል አለባት ማለታቸው ተገለጸ፡፡

ልዑሉ የፍልስጤም አመራሮችን በመተቸት ወቀሳቸውን በመተው እንዲሁም ያለውን ሁኔታ ተቀብለው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ያቀረበላቸውን ዕቅድ መቀበል አለባቸው ብለዋል፡፡

ይህንን ያሉት ባለፈው ወር በኒውዮርኩ ጉብኝታቸው ሲሆን፥ ተቀማጭነታቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ካደረጉ የአይሁድ አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ነው ተብሏል፡፡

ውይይታቸውም በዝግ ስብሰባ መካሄዱን የእስራዔል ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

ልዑሉ ባላፉት ዓመታት የፍልስጤም አስተዳደር የቀረቡለትን አብዛኛዎቹን የሰላም ስምምነቶችን በተደጋጋሚ ውድቅ ማድረጉን አንስተው፥ አሁን በትራምፕ የቀረበው ዕቅድ ላይ መስማማት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በዚህ የስምምነት ማዕቀፍ ውስጥ ማለፍ የማይችሉ ከሆነ አርፈው መቀመጥ አለባቸው ስለማለታቸው ተነግሯል፡፡

ሆኖም የሳዑዲ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ እስከአሁን ያሉት ነገር የለም፡፡

 

ምንጭ፦አልጀዚራ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram