fbpx
AMHARIC

ፌዴሬሽኑ በወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ቅጣት ላይ ማሻሻያ አደረገ

የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ አምስት ተጫዋቾች ላይ ተጥሎባቸው የነበረው እገዳ እንደተነሳለቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የፌዴሬሽኑ ዲስፕሊን ኮሚቴ እንዳስታወቀው በወልዋሎ ተጫዋቾች በረከት ተሰማ ፣ አለምነህ ግርማ፣ማናየ ፋንቱ እና አፍወርቅ ሀይሉ ላይ ተጥሎ የነበረው የስድስት ወር እገዳ እና የ10 ሺህ ብሩ ቅጣት ተነስቶ ወደ ከባድ የፁህፍ ማስጠንቀቂያ ተቀይሯል።

በተጨማሪም የዋለልኝ ገብሬ የሁለት ዓመት እገዳ እና የ15ሺህ ብር ቅጣት ተሽሮ የአምስት ሺህ ብር ቅጣት እና ከባድ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው ተደርጓል።

በሌላ በኩል  በረከት አማረ ተጥሎ የነበረው የስድስት ወር እገዳ እና የ10ሺህ ብር ቅጣት የፀና ሲሆን፥ የአስሪ አልማህዲ የስድስት ወር እገዳ እና የ10ሺህ ብር ቅጣት ደግሞ ወደ አንድ ዓመት እና 20 ሺህ ብር ቅጣት እንደተሻሻለ ነው የዲስፕሊን ኮሚቴው ያስታወቀው።

በክለቡ ቡድን መሪ በነበሩቱ በአቶ ማሩ ገብረፃዲቅ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጣለባቸው የእድሜ ልክ እገዳ ፣ በወልዋሎ ክለብ የተጣለው በፎርፌ መሸነፍ እና የ250 ሺህ ብር ቅጣት መፅናቱ ታውቋል። ኤፍ ቢ ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram