fbpx
AMHARIC

ፌስቡክ የስልክ ንግግር እና የጽሁፍ መልእክት ኢንፎርሜሽኖች የተጠቃሚውን ፍቃድ የሚጠይቁ ናቸው ብሏል

የማህበራዊ ሚዲያ ኔትወርኩ ፌስቡክ (Facebook) ከተለያዩ የቴክኖሎጂ ተቋማት እና ሚዲዎች የተጠቃሚዎች የስልክ ልውውጥ እና አጭር የጽሁፍ መልእክቶች ጋር እየተነሱ ላሉ ሪፖርቶች ምላሽ ሰጠ፡፡

የስልክ ልውውጥ ሆነ አጭር የጽሁፍ መልእክቶችን ያለ ተጠቃሚው ፍቃድ ማንኛውም አይነት ህገወጥ ተግባር እንደማያከናውን ኩባንያው አሳውቋል፡፡ 
ሆኖም የማህበራዊ ሚዲያ ተቋሙ የመረጃ መጫኛ አማራጭ በተጠቃሚው ፍቃድ የሰጠ (enabled) ከሆነ እና ኢንፎርሜሽኑ ከተጫነ ፕላትፎርሙ በፌስቡክ ላይት (Facebook Lite) እና በፌስቡክ በሚሴንጀር (Facebook Messenger) የተከናወኑ አጭር የጽሁፍ መልክቶችን እና የስልክ ንግግር መረጃዎችን እንደሚጠቀም አሳውቋል፡፡

ከዚህ ውጪ ሚስጥራዊ የግለሰብ የጥሪዎችን እና አጭር የጽሁፍ መልእክቶችን እንደማያከማች እና ለሶስተኛ ወገን እንደማይሸጥ ፌስቡክ መበግለጫው አሳውቋል፡፡


ምንጭ፤- ሮይተርስ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram