ፌስቡክና ኢንስታግራም የመተግበሪያ አጠቃቀም ሰዓት ላይ ገደብ ማስቀመጥ የሚያስችል አዲስ ገፅ ይፋ አደረጉ
ፌስቡክና ኢንስታግራም ሰዎች የመተግበሪያ አጠቃቀማቸው ላይ የሰዓት ገደብ ማስቀመጥ እንዲችሉ የሚረዳ አዲስ ገፅ ይፋ ማድረጋቸው ተገለፀ።
ይህ አዲሱ ገፅ ሰዎች ፌስቡክን እና ኢንስታግራምን በሚጠቀሙበት ወቅት ምን ያህል ሰዓት እንደተጠቀሙ የሚያሳይ መልዕክት እንደሚያደርሳቸው ታውቋል።
የፌስቡክ ኩባንያና በስሩ የሚገኘው ኢንስታግራም አዲስ ይፋ ያደረጉት ገፅ ሰዎች በመተግበሪያዎች ላይ ያሳለፉትን ሰዓት መቆጣጠር እንዲችሉ ያደርጋል።
እንዲሁም ሰዎች በቀን ውስጥ መጠቀም የሚፈልጉትን የሰዓት ገደብ እንዲያስቀምጡ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።
አዲሱ የሰዓት መገደቢያ የፌስቡክ ገፅ ሰዎች ምን ያህል ሰዓት እንደተጠቀሙ የሚያሳውቃቸው መልዕክት እንዲደርሳቸው ያደርጋልም ተብሏል።
ምንጭ፦ ሲኤንኢቲ
Share your thoughts on this post