fbpx
AMHARIC

ጤነኛ ጥርስ ፈገግታን ከማሳመር በዘለለ ስለ አጠቃላይ የጤናችን ምን ይጠቁመናል?

የጥርስን ጤንነት መጠበቅ ፈገግታን ከማሳመር በላይ ስለ አጠቃላይ የጤንነታችን ሁኔታ የሚለን ነገር አለ ይላሉ ተመራማሪዎች።

በአጠቃላይ የአፋችንን ጤንነት በተለይ የጥርስን ጤንነት አጠቃላይ ጤናችን ምን ይመስላል የሚለውን ለመለየት እንዴት ይጠቅማል በሚለው ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶች ሲሰሩ ቆይተዋል።

ከዚህ በፊት ከተሰሩ ጥናቶች ውስጥም አንዳንድ የጥርስ ህመሞች ለስኳር በሽታ መጋለጣችንን ምልክት የሚሰጡ መሆኑ ተጠቅሷል።

የተወሰኑ የጥርስ ህመሞች ደግሞ ለስትሮክ (ወደ አእምሯችን የሚገባው ደም መቋረጥ ወይም መቀነስ) የጤና ችግር ተጋላጭነት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት እየተሰራ ያለው ጥናት ደግሞ ከእድሜያችን ጋር ተያይዞ ጥርሳችን ያለብት ሁኔታ ከልብ ጤንነት ጋር ምን አይነት ግንኙነት አለው በሚለው ላይ የሚያጠነጥን ነው።

የአሜሪካ ኒው ኦርሊያንስ ቱላን ዩኒቨርሲቲና በቦስተን ሀርቫርድ ቲ.ኤች ቻን የህብረተሰን ጤና ትምህርት ቤት በጋራ እያካሄዱት ያለው ጥናት በመካከለኛው የእድሜ ክልል የሚከሰት የጥርስ መነቀል እና መሰባበር ላይ ያተኮረ ነው።

በጥናቱ ላይ እድሜያቸው ከ45 እስከ 69 መካከል የሚገኙ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ ጥርሳቸው መነቀል አለመነቀሉ እንዲሁም ከተነቀለ ደግሞ በስንት ዓመት ልዩነት የሚለው ላይ ክተትል አድርጓል።

በተሳታፊዎች ላይ ክትትል መደረግ ከተጀመረ በኋላም ከተሳታፊዎቹ ውስጥ በ8 ዓመት ውስጥ አንድ ጥርስ እንደተነቀለባቸው አስታውቀዋል።

ጥናቱ ከተጀመረ ከ12 እስከ 18 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ አንድ እና ሁለት ጥርስ የተነቀለባቸው ተሳታፊዎች እንዳሉ ነው አጥኚዎቹ የገለፁት።

ተመራማሪዎቹ ባደረጉት ክተተልም በመካከለኛው የእድሜ ክልል ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ ጥርሳቸው የተነቀለባቸው ሰዎች ከከፍተኛ የልብ ህመም ተጋላጭነት ጋር ግንኙነት እንዳለው ለይተዋል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Health

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram