fbpx
AMHARIC

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ ከሮቦቷ ሶፍያ ጋር ቆይታ አደረጉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሶፍያ ከተባለችው ሮቦት ጋር በዛሬው እለት ቆይታ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአይ.ሲ.ቲ ኤክስፖ ኢትዮጵያ 2010 ላይ የተገኘችውን ሮቦቷን ሲፊያ ነው በዛሬው እለት ያገኙት።

ሶፊያ የተባለችው ሮቦት 67 በመቶ ፕሮግራም የተደረገችው እና የተሰራቸው በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ነው።

በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ሶፍያን እውን በማድረግ ሂደት ጉልህ ድርሻ በነበራቸው ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች ስራ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ሶፊያ የተባለችው ሮቦት 67 በመቶ ፕሮግራም የተደረገችው እና የተሰራቸው በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መሆኑን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ የመለክታል።

ሮቦቷ ሶፊያ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይም የሳዑዲ አረቢያን ሙሉ ዜግነት ማግኘቷ ይታወሳል።

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች 67 በመቶ ፕሮግራም የተደረገችውና ከሰው ጋር ተመሳስላ የተሰራቸው ሮቦቷ ሶፊያ በሆንግ ኮንጉ ሃንሰን ሮቦቲክስ ኩባንያ ነው የተፈበረከችው።

በዓለም ላይ ከተሰሩ ሰው መሰል ሮቦቶች ሶፍያ የሰው እሳቤ የበለጠ የተንፀባረቀባት የፈጠራ ሮቦት ነች።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram