fbpx
AMHARIC

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የፊታችን ሰኞ ሀምሌ 16 2010 ዓ.ም ነው ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ውይይቱ ላይም ከ45 የመንግሰት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና 4 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተወጣጡ 3 ሺህ መምህራን እንደሚሳተፉም ተገልጿል።

በመድረኩም በተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ እና ምሁራን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት የሚካሄድ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

የውይይት መድረኩንም የትምህርት ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑንም ገልጿል።

የትምህርት ተቋማቱ መምህራንን በጾታ፣በትምህርት አይነትና በደረጃ አመጣጥነው መርጠው እንዲልኩ እና ተቋማቱ የተመሰረቱበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ ኮታ እንደተሰጣቸውም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram